“ኢትዮጵያ የተመድን ሰራተኞች ለማባረር መወሰኗን በመስማቴ ደንግጫለሁ”-አንቶኒዮ ጉቴሬዝ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ኢትዮጵያ የድርጅቱን ከፍተኛ ሰብዓዊ አስተባባሪዎች ጨምሮ ሰባት የድርጅቱን ሰራተኞች ለማባረር መወሰኗን በመስማቴ ደንግጫለሁ ሲሉ አስታወቁ፡፡
ዋና ጸሃፊው ሁኔታውን በማስመልከት በቃል አቀባይ ጽህፈት ቤታቸው በኩል መግለጫ አውጥተዋል፡፡
በመግለጫው “ኢትዮጵያ የድርጅቱን ከፍተኛ ሰብዓዊ አስተባባሪዎች ጨምሮ ሰባት የድርጅቱን ሰራተኞች ለማባረር መወሰኗን በመስማቴ ደንግጫለሁ” ብለዋል።
ሁሉም ሰብዓዊ ተግባራት በሰብዓዊነት፣ ያለ አድልዖ፣ በነጻ እና ገለልተኛነት መርሆዎች የሚመሩ ናቸው ያሉ ሲሆን ድርጅታቸው በኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒቶችን ጨምሮ ህይወት አድን ድጋፎችን እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡
ጉተሬዝ በመግለጫቸው “ይህን በሚሰሩ የኢትዮጵያ ስታፍ አባላት ሙሉ መተማመን አለኝ” ብለዋል፡፡
ድርጅታቸው ሰብዓዊ ድጋፍ የሚሹ ኢትዮጵያውያንን ለመርዳት ቁርጠኛ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ሰራተኞቹ ስራቸውን በሚቀጥሉበት ሁኔታ ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመነጋገር ላይ መሆናቸውንም ዋና ጸሃፊው አስታውቀዋል፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም