Ticker

6/recent/ticker-posts

የአፍሪካ ልማት ባንክ ሁሉንም አለም አቀፍ ሰራተኞቹ ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ወሰነ

 


የአፍሪካ ልማት ባንክ ሁሉንም አለም አቀፍ ሰራተኞች ከኢትዮጵያ በአስቸኳይ እንዲወጡ ወስኗል።

 

ባንኩ ይህን የወሰነው ያለ ክስ እና ማብራሪያ ለሰዓታት ታስረው በመደብደባቸው ነው፡፡

 

እንደ ባንኩ ጋዜጣዊ መግለጫ ውሳኔው የተላለፈው ባለፈው ወር በአዲስ አበባ በሚገኙ የአፍሪካ ልማት ባንክ በሁለት የአለም አቀፍ የስራ ባልደረቦች ላይ የዲፕሎማቲክ ፕሮቶኮሎችን በመጣስ የኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች ያደረሱትን ጥቃት ተከትሎ ነው።

 

የባንኩ ፕሬዝዳንት አኪንዉሚ አደሲና (ዶ/ር) በጉዳዩ ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣኖችን ጋር ከተነጋገሩ በኋላ የባንኩ ሁለት ሰራተኞች ከእስር ተለቀዋል። ሆኖም ጥቃት አድራሾቹ ተጠያቂ አልሆኑም፡፡

 

ውሳኔው አጣብቂኝ ውስጥ ለገባችው ኢትዮጵያ ፈታኝና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን የሚጎዳ ነው፡፡

 

የባንኩ ጥሪ በአገር አቀፍ ደረጃ በተቀጠሩ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ላይ ተፅዕኖ አይኖረውም ብሏል፡፡


አስተያየት ይለጥፉ

0 አስተያየቶች