ትናንት (ሰኞ ታህሳስ 25) በቦሌ አየር ማረፊያ VIP ሳሎን አቀባበል የተደረገለት እና በመንግስት ሚድያዎች "ፓን አፍሪካኒስት" ተብሎ የተገለፀው ሎንታታ ላክስ ማን ነው?
ትናንት ከኢቢሲ እስከ ፋና፣ ከኢዜአ እስከ አዲስ ሚድያ ኔትዎርክ ወዘተ ያሉ ሚድያዎች "ፓን አፍሪካኒስቱ" እንዲሁም "ደቡብ አፍሪካዊው የማህበረሰብ ንቅናቄ መሪ" ብለው የጠሩት ሎንታታ ላክስ አዲስ አበባ ገብቷል፣ የመንግስት ሀላፊዎችም በቦሌ አየር ማረፊያ ተገኝተው በVIP ሳሎን አቀባበል አርገውለታል።
ይሁንና ግለሰቡ "አፍሪካውያን ከሀገራችን ደቡብ አፍሪካ ለቀው ይውጡልን" በሚለው አቋሙ የሚታወቅ ነው፣ በቅርብ አመታት በደቡብ አፍሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ሌሎች አፍሪካውያን ላይ ጥቃት ሲደርስ ሎንታታ ላክስ እና መሰለቹ ተባባሪ እንደነበሩ ይታወሳል።
ይህ ከታች የሚታየው ስክሪንሾት የተወሰደው ግለሰቡ ዛሬ ጠዋት እዚሁ አዲስ አበባ እንዳለ ኢንስታግራም እና ትዊተር ላይ ከፃፈው ላይ ሲሆን አፍሪካውያንን "ወደ ሀገራችሁ ተመለሱ" ያለ ሲሆን "ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚደረግ ህገ-ወጥ ስደት የኔኦ-ኮሎኒያሊስቶች ሴራ ነው" ብሏል።
ታድያ ይህንን ሰው ነው "ማህበራዊ ፍትህን ለማስፈን በሚያደርገው ትግል የሚታወቀው ደቡብ አፍሪካዊው የማህበረሰብ ንቅናቄ መሪ" ብለው የመንግስት ሚድያዎች ለህዝብ ያቀረቡት።
ኧረ በዜና የምታቀርቡትን እና አቀባበል የምታደርጉትን ግለሰብ እንኳን መጀመርያ አጣሩ! እባካችሁ ስለዚህ ትልቅ ህዝብ እና ሀገር ብላችሁ!
ሙሉ ፅሑፉ የጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ነው።
0 አስተያየቶች