የቀድሞ የኢሳት ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ እስካሁን ፍርድ ቤት አለመቅረቡንና የት እንዳለ አለመታወቁን ጠበቃው ገለፁ ።
ያለፈው ዕሁድ በመንግስት አካላት ለጥያቄ ትፈለጋለህ ተብሎ መወሰዱ የተገለፀው ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ እስካሁን ፍርድ ቤት አለመቅረቡንና ያለበት ቦታም እንደማይታወቅ የጋዜጠኛው ጠበቃ አዲሱ አልጋው ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል።
ጠበቃው አያይዘውም ጋዜጠኛው የታሰረበትን ቦታ ለማወቅ የአዲስ አበባንና የፌደራሉን ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ መጠየቃቸውን ገልፀው፤ ነገር ግን የለም መባላቸውን ተናግረዋል።
በመሆኑም መንግስት በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጥበት ጠበቃው አሳስበዋል።
ያካልሆነ እና ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ያለበት ወቅታዊ ሁኔታ የማይገለፅ ከሆነ ጉዳዩን ወደ ፍትሕ ሚኒስቴር እንደሚወስዱት አመልክተዋል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጋዜጠኛው የት እንደታሰረ እንደማይታወቅ እና ጉዳዩ እንዳሳሰበው መግለፁ ይታወቃል።
ጎበዜ ሲሳይ ከዚህ ቀደም በኢሳት ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ተቀጥሮ ይሳራ ነበር።
ከሰሜኑ ጦርነት ጋር በተያያዘ በሰሜን ወሎ በኩል ስለነበረው ክስተት በማህበራዊ ገፁ ማጋራቱን ተከትሎ ጋዜጠኛው ከስራ ታግዶ ነበር። ቀጥሎም በዩትዩብ አማካኝነት መረጃዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል።
የጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይን እስር በተመለከተ ከመንግስት እስካሁን የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ የለም፡፡
0 አስተያየቶች