የህወሓት ኃይሎች በመጋዘኖች የነበረ የእርዳታ እህል መዝረፋቸውን የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ገለጸ
የህወሓት ኃይሎች ባለፉት ቅርብ ሳምንታት የአሜሪካ መንግሥት ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤይድ) የሆኑ የእርዳታ መጋዘኖችን መዝረፋቸው
ተገለጸ።
የድርጅቱ
የኢትዮጵያ ተልዕኮ ዳሬክተር ሾን ጆንስ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ እንደተናገሩት የህወሓት ኃይሎች በደረሱባቸው ስፍራዎች
የሚገኙ የእርዳታ መጋዘኖችን ዘርፈዋል።
የአሜሪካ
ተራድኦ ድርጅት የኢትዮጵያ ተልዕኮ ዳይሬክተር ሾን ጆንስ "ወታደሮችና የታጠቁ ሰዎች ከዜጎች ምግብ ሰርቀዋል። በተለይ ህወሓት
በገባባቸውና ጦርነት በከፈተባቸው ሁሉም የአማራ አካባቢዎች መጋዘኖችን ዘርፏል፤ ተሽከርካሪዎች ዘርፏል። ውድመት ፈፅሟል"
ብለዋል ዳሬክተሩ።
በትግራይ
ክልል በፌደራሉ መንግሥት እና በህወሓት ኃይሎች መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን መግደሉ እና ከፍተኛ የሰብዓዊ
ቀውስ ስለመፍጠሩ ተዘግቧል።
የዩኤስኤይድ
የኢትዮጵያ ተልዕኮ ዳሬክተር ሾን ጆንስ ለኢቢሲ ሲናገሩ፤ "በተለይ የህወሓት ኃይሎች በገቡባቸው የአማራ ክልል አካበቢዎች
በርካታ የእርዳታ መጋዘኖቻችን ስለመዝረፋቸው እና መጋዘኖቹ ባዶ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ አለን" ብለዋል።
ዳሬክተሩ
አክለውም "ህወሓት ሁኔታዎችን ያለአግባብ እየተጠቀመ እንደሆነ አምናለሁ። ከተረጂዎች ላይ በኃይል እርዳታ እየነጠቀ እንደሆነ
ይሰማናል፤ የምናውቀው ሃቅ ግን የህወሓት ኃይሎች በገቡባቸው አካባቢዎች ሁሉ የእርዳታ መጋዘኖቻችን ዘርፈዋል" ብለዋል።
ባለፈው
ሳምንት በተባበሩት መንግሥት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ውስጥ የአሜሪካ ተወካይ በተመሳሳይ "በአማራ ክልል ውስጥ የእርዳታ
መጋዘን በህወሓት ኃይሎች መዘረፉን" ተናግረው ነበር።
በተጨማሪም
ከቀናት በፊት ዩኤስኤይድ ለህወሓት የኃይል ሰጪ ምግብ እርዳታ እየሰጠ ነው የሚለውን ክስ ውድቅ ባደረገበት መግለጫው ላይ
"በአብዛኛውን ጊዜ በግጭት አካባቢዎች ታጣቂዎች እርዳታ ከሚፈልጉ ሰዎች እንደሚሰርቁ" አመልክቶ ነበር።
የአሜሪካ
ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅት የኢትዮጵያ ተልዕኮ ዳሬክተር ይህን ማለታቸውን ተከትሎ የህወሓት አመራሮች እና የፌደራሉ መንግሥት
በጉዳዩ ላይ እስካሁን ያሉት ነገር የለም።
ከዚህ
ቀደም የህወሓት አማጺያን እና የፌደራሉ መንግሥት የሰብዓዊ እርዳታ ፍሰትን በማደናቀፍ እርስ በርስ ይወቃቀሳሉ።
የፌደራሉ
መንግሥት በተደጋጋሚ የህወሓት ኃይሎች ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ የሰብዓዊ እርዳታ ቁሶች ወደ ክልሉ እንዳይገቡ እንቅፋት እየሆነ
ነው እንዲሁም ዘረፋ ይፈጽማል ሲል ቆይቷል።
የህወሓት
አመራሮች በበኩላቸው የፌደራሉ መንግሥት የሰብዓዊ እርዳታ ትግራይ እንዳይደርስ መንገዶችን ዘግቷል ሲሉ ይከሳሉ።
ሾን ጆንስ
"ማንኛውም የሰብዓዊ እርዳታ ጣልቃ ገብነት ወይም ስርቆት ተቀባይነት የሌለውና ለተቸገሩ ሰዎች እርዳታ እንዳይደርስ የሚያደርግ
ነው" ብለዋል።
በትግራይ
ወደ 900 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በርሃብ ሁኔታ ውስጥ ሲሆኑ፤ ሌሎች 5 ሚሊየን የሚሆኑት ደግሞ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል
ብሏል የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት።
ባለፉት
ሁለት ወራት ወደ አማራና አፋር ክልሎች በተስፋፋው ጦርነት ምክንያት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ተጨማሪ ሰዎች በሁለቱ ክልሎች ውስጥ
ተፈናቅለው እርዳታ እንደሚሹ ክልሎቹ መግለጻቸው ይታወቃል።
በዘጠኝ
ወራቱ የጦርነት ወቅት ለመጀመሪያ ጊዜ የእርዳታ ሠራተኞች በሚሊየን ለሚቆጠሩ ሰዎች ለመድረስ የምግብ ክምችት እንደሚያልቅባቸው ባለፈው
ሳምንት የዩኤስኤይድ ኃላፊ መናገራቸው ይታወሳል።
የአሜሪካ
ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤይድ) በኢትዮጵያ ውስጥ በሚካሄደው ህይወት አድን ምግብ እና እንክብካቤ አቀርቦት ዋነኛ ከሚባሉት
መካከል የሚመደብ ነው።
ድርጅቱ
እንደሚለው በአሁኑ ጊዜ በመላው አገሪቱ ካለው ሕዝብ 7 በመቶ ለሚሆኑ የኢትዮጵያ ዜጎች የምግብ እርዳታ በማቅረብ ድጋፍ እየሰጠ
ይገኛል።
ምንም አስተያየቶች የሉም