የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ባንክ የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር የንግድ ባንኮችን የጥሬ ገንዘብ መጠባበቂያ ጥምርታ በእጥፍ ማሳደጉን አስታወቀ
![]() |
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሕንፃ |
ሮይተርስ ከአዲስ አበባ እንደዘገበው ከመስከረም 1 ቀን 2021 ጀምሮ ባንኮች ከሚሰበሰቡት የተጣራ ቁጠባ በኢትዮጵያ ማዕከላዊ ባንክ እንዲያስቀምጡ የሚገደዱትን የመጠባበቂያ መጠን ከ5 በመቶ ወደ 10 በመቶ ከፍ ተደርጓል፡፡ የንግድ ባንኮችም ለአጭር ጊዜ ብድር ለማዕከላዊ ባንክ የሚከፍሉት ወለድ ከ 13% ወደ 16% ማደጉን የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ባንክ ትናንት ባውጣው በመግለጫ አመልክቷል።
አበዳሪዎችም፤ ከላኪዎች እና ከእርዳታ ድርጅቶች የሚያገኙትን የውጭ ምንዛሬ ድጋፍ ወደ ማዕከላዊ ባንክ እንዲያቀርቡ የሚጠየቁት ከ30 በመቶ ወደ 50 በመቶ ከፍ ብሏል።በኢትዮጵያ የዕዝና እና የቁጥጥር ኢኮኖሚ ውስጥ መንግሥት የባንኮችን የውጭ ምንዛሪ ምደባ ይቆጣጠራል ሲልም ዘገባው አክሏል።
እንደ ማዕከላዊ ባንክ ይህ ድንጋጌ የመንግስትን የውጭ ምንዛሬ የገቢ በማሳደግ የውጭ ዕዳን የመክፈል አቅም የሚጨመር ነው።ከዚህ በተጨማሪ እርምጃው የመሠረተ ልማት ግንባታዎች እና የመሠረታዊ ሸቀጦችን ወደ ሀገር የማስገባት አቅምን ያሳድጋል ተብሏል ።
እንደ ሮይተርስ ዘገባ በሀገሪቱ ዓመታዊ የዋጋ ግሽበት በሐምሌ ወር 26.4% የነበረ ሲሆን፤ ዓመቱን ሙሉ ግን የግሽበት መጠኑ ወደ 20% የተጠጋ ነበር። ይህም መንግሥት ችግሩን ለመግታት የሚያደርገውን ጥረት የሚጣረስ ነው ብሏል።
የቻይናው ኤግዚም ባንክ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ብድር መስጠት እያደገ የመጣውን የውጭ ዕዳ እና የመክፈል ችግሮች ሊያባብሰው ይችላል በሚል፤ ወደ 339 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ብድር ማገዱን አንድ የኢትዮጵያ የመንግስት ባለሥልጣን በዚህ ወር መናገራቸው ይታወሳል።
ምንም አስተያየቶች የሉም