ተሰብሮ የነበረው የተከዜ ድልድይ ተገንብቶ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
![]() |
በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል በትግራይ ክልል የሚገኘው የተከዜ ድልድይ ተገንብቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
ከመቶ ሜትር በላይ ርዝመት ያለው ድልድዩ ሽሬ ከተማን ከማይፀብሪ ጋር የሚያገናኝና አገልግሎት
በመስጠት ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ ነው፡፡
ባለፈው ጥቅምት 24 የፌደራሉ መንግሥት የሰሜን ዕዝ በህወሓት ጥቃት እንደደረሰበት
ገልፆ ‹‹ሕግን የማስከበር›› ባለው ጦርነት ምክንያት በተካሄደው ውጊያ ምክንያት ነበር ድልድዩ ሊሰበር የቻለው፡፡
ምንም እንኳን ድልድዩ በጦርነቱ ምክንያት ቢሰበርም በማን ምክንያት እንደተሰበረ ግን
በግልፅ አልታወቀም፡፡
በትግራይ ክልል መንግሥት የሚተዳደረው የትግራይ ቴሌቪዥን በምስል አስደግፎ ባወጣው ዘገባ
ላይ ድልድዩ እንደገና ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
ሁለት ወራት ገደማ ከአገልግሎት ውጭ በመሆኑ በክልሉ ያሉ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚሹ
ዜጎችን ጉዳት የከፋ እንዳደረገው የእርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ሲገልፁ ቆይተዋል፡፡
የቴሌቪዥን ጣቢያው ድልድዩ በራስ አቅም ተገንብቷል ቢልም የጥራት ሁኔታውንና ምን ያህል
ወጪ እንደተደረገበት ግን ያለው ነገር የለም፡፡
በትግራይ ክልል የተጀመረው ጦርነት የውጭ ሃገራት በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተሳትፈውበት በርካቶችን
ለህልፈተ ሕይወትና ለጉዳት አጋልጦ ወደ አማራና ዓፋር ክልሎች ተስፋፍቷል፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም