አየርላንድ የጸጥታው ምክር ቤት የመስከረም ወር ሰብሳቢነትን ከህንድ ተረከበች
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት የወርሃ መስከረም
ሰብሳቢ አየርላንድ ሆና ተመረጠች፡፡
ተ.መ.ድ. በትግራይ ክልል ጉዳይ ስምንት ጊዜ እንዲወያዩ ካደረጉ
ሃገራት መካከል አንዷ የሆነቺው አየርላንድ ሰብሳቢነቱን ከህንድ ነው የተረከበችው፡፡
የወርሃ ነሃሴ የምክር ቤቱ ሰብሳቢ የነበረችው ህንድ ምክር ቤቱ
በትግራይ ጉዳይ በተወያየበት ጊዜ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ‹‹ጣልቃ መገባት የለበትም›› ስትል በመቃወም ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን
መቆሟ የሚታወስ ነው፡፡
ወቅታዊ የኢትዮጵያን ሁኔታዎች በአሳሳቢነት ስትገልጽ የሰነበተችው
አየርላንድ በበኩሏ ከአሁን ቀደም ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ አስቸኳይ ስብሰባን እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረቧ የሚታወስ ነው፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም