በሙሼ ሰሙ (የምጣኔ ኃብት ባለሙያ)
በሀገራችን ኢኮኖሚ ዙርያ ብዙ ነገር ስለተባለና ብዙ ነገር ስለተመሰቃቀለ ብዙ ማለት በተገባ ነበር። ነገር ግን የቱን አንስቶ የቱን መተው ይቻላል። የዘገየሁ ቢሆንም እስኪ ጊዜ እስኪፈቅድ ድረስ ከእለት እንጀራችን ልጀምር።
ዛሬ ሲኤምሲ አደባባይ ከሚገኘው ብለስ ዳቦ ቤት አንድ ዳቦ 8 ብር ገዝቼያለሁ። በተቃራኒው የዛሬ ዓመት በተመሳሳይ ጊዜ አንድ ዳቦ ከዚሁ ዳቦ ቤት በ 4 ብር መግዛት ችዬ ነበር። የዛሬ ሳምንት ደግሞ 6 ብር ገዝቼ ነበር።
ገዥው ፖርቲ በሁለት ዓመት ውስጥ ስንዴ ኤክስፖርት ለማድረግ ቢያቅድም የስንዴ ምርት አንድ ዓመት ቀድሞ አስተማማኝ የአቅርቦት ደረጃ ላይ መድረሱን ሰምተናል። በዚህ ምክንያትም ከእቅዱ አንድ ዓመት ቀድሞ ብሎ ስንዴ ኤክስፖርት ማድረግ የሚችልበት ደረጃ ላይ የመድረሱን ዘገባ አጣጥመን ሳንጨርስ የዳቦ ዋጋ ከዛሬ ዓመት ዋጋው ላይ 100 % የጨመረ ሲሆን ከዛሬ ሳምንት ዋጋ
ላይ ደግሞ ከዛሬ ሳምንት ዋጋው ላይ
33.33 % ጨምሯል።
ኢትዮጵያም በዓለም ላይ ከሚገኙ ሀገራት መካከል በአንድ ቅርጫት የተለያዮ ቁሶች የምርት አቅርቦት ዋጋ (Basket of good) ላይ በግሽበቷ ምጣኔ መሰረት 10ኛ ሀገር ሆናለች።
ከወር እስከ ወር ግሽበቷ ከ 2%
በላይ እየጨመረ ነው። አሁን ላይ የዓለም አማካይ ግሽበት ከ 5 እስከ 7 በመቶ መሆኑ እየተመዘገበ ነው። መረጃ መተንተን ቢያቅተን እንኳን ከነባራዊ ሁኔታ ተነስተን መገመት ይሳነን። ወገን ነገሩ እንዴት ነው !?
ከነዳጅ ዋጋ ጭማሪ በኋላስ ምን ይውጠን ይሆን?!
0 አስተያየቶች