የ96 ዓመቷ የብሪታንያ እና የኮመን ዌልዝ አገራት ንግሥት ኤልሳቤጥ ዳግማዊት አረፉ።
ንግሥቲቱ ማረፋቸውን የባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት ይፋ አድርጓል።
ቀደም ሲል ሐኪሞች የንግሥቲቱ ጤና በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ ነው ብለው ነበር።
የንግሥቲቱ የጤና ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ተከትሎ በርካርታ የንጉሣውያን ቤተሰብ አባላት ንግሥቲቱ ወደሚገኙበት ስኮትላንድ ባልሞር ቤተ-መንግሥት አቅንተው ነበር።
ንግሥት ኤልሳቤጥ ዳግማዊት በ70 ዓመት የንግሥና ዘመናቸው በርካታ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ለውጦችን ተመልክተዋል።
የንግሥቲቱን የጤና አሳሳቢ መሆን ዜና ከተሰማ በኋላ በርካታ ፖለቲከኞች እና ተዋቂ ግለሰቦች በዜናው መረበሻቸውን ሲገልጹ ነበር።
ንግስት ኤልዛቤጥ ወደ ንግሥናው የመጡት እአአ 1952 ነበር። ንግሥቷ በ70 ዓመታት የንግስና ዘመናቸው በብሪታንያ እና በመላው ዓለም ብዙ ማሕበራዊ ለውጦች ተከናውነዋል።
0 አስተያየቶች