Ticker

6/recent/ticker-posts

ቤተክርስቲያን ውስጥ ምዕመናንን የገረፈው ነብይ ታሰረ



ነብይ መሆኑን የሚናገረውና ተከታዮችም የመሰከሩለት ኡጋንዳዊ ኪንቱ ዴኒስ በቤተ ክርስቲያኑ አባላት ላይ አካላዊ ጥቃትን በመፈጸም እንዲሁም በሰዎች ዝውውር ታስሮ ክስ ቀረበበት።


"ነብይ" ኪንቱ ዴኒስ የተከሰሰው የ‘ሆይማ ኢምፓወርመንት’ ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን አባላትን በበትር ሲገርፍ የሚያሳይ ቪዲዮ በኢንተርኔት ላይ በስፋት ከተሰራጨ በኋላ እንደሆነ ቢቢሲ ዘግቧል።


የኡጋንዳ ፖሊስ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የታየውን ተንቀሳቃሽ ምስልን ተከትሎ በቀረበው አቤቱታ መሠረት የ42 ዓመቱን "ነብይ" እና ሌሎች አራት ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል።


በስፋት በታየው ቪዲዮ ላይ ነብይ ኪንቱ የቤተ ክርስቲያኑን ሌሎች አባላትን ወደ ፊት መጥተው እንዲገረፉ ካልሆነም በፀሎት ሥነ ሥርዓት ላይ እና በሌሎች አገልግሎቶች ላይ የመሳታፍ ዕድልን እንደማያገኙ ሲናገር ይሰማል።


ከዚያም በቤተክርስቲያኑ የተሰበሰበው ምዕመን ከአባላቱ መካከል አንድ በአንድ ወደ ፊት እየቀረቡ ሲገረፉ ሲመለከቱ የሚታይ ሲሆን፣ ከበስተጀርባም ለስላሳ የፒያኖ ድምጽ ይሰማል።  


በፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋለው "ነብይ'' ኪንቱ በምርመራ ወቅት እንደተናገረው፣ በተንቀሳቀቃሽ ምስሉ ላይ የሚታየው በበትር መገረፍ ትዕይንት የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርትን ምሳሌን መሠረት ያደረገ ነው ብሏል።


በዚህም ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተ መቅደስ ውስጥ ሸቀጦችን ሲነግዱ የነበሩትን ሰዎች እንዴት አድርጎ በጅራፍ እየገረፈ እንዳስወጣቸው የሚያሳየውን ሁኔታ በተግባር ለማሳየት የተደረገ መሆኑን መናገሩን የፖሊስ መግለጫ አመልክቷል።

       

For daily News Visite Agelgl Media  


ይህንንም ክስተት ተከትሎ የኡጋንዳ ባለሥልጣናት ግለሰቡ በሕገ ወጥ መንገድ ሥራውን እያከናወነ ነው ሲሉ ከሰውታል።


ክሱን ተከትሎ ፖሊስ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ባደረገው ፍተሻ በቪዲዮው ላይ በምዕመናኑ ላይ በተፈጸመው ግርፋት ጥቅም ላይ የዋሉ ሳይሆኑ አይቀሩም የተባሉ ሦስት በትሮች መገኘታቸው ተነግሯል።


ነብይ ኪንቱ ዴኒስ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራው አስከሚጠናቀቅ ድረስ አስከ መጪው ሐሙስ ጳጉሜ 1 ድረስ በእስር ላይ እንደሚቆይ ተገልጿል።


በኡጋንዳ ውስጥ በርካታ የኢቫንጀሊካል አብያተክርስቲያናት በመላው አገሪቱ የሚገኙ ሲሆን፣ አብዛኞቹ በሕግ ያልተመዘገቡ እና ብዙዎቹ ደግሞ እራሳቸውን የአግዚአብሔር ሰው አድርገው በሰየሙ ግለሰቦች የሚመሩ እንደሆነ ተነግሯል።


በተመሳሳይ  በኢትዮጵያም ሰዎችን ለጤና ችግር የሚዳርግ ትዕዛዝ የሚሰጡ በርከት ያሉ ተከታዮች ያሏቸው "ነብዮዎች" መመልከት እየተለመደ መጥቷል።


For daily News Visite Agelgl Media  

አስተያየት ይለጥፉ

0 አስተያየቶች