Ticker

6/recent/ticker-posts

በሱዳን የሚኖሩ ኢትኢትዮጵያዉያንና ኤርትራውያን በጅምላ እየታሰሩ ነው

በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በጅምላ እየታሰሩ ነው


በሱዳን የሚኖሩ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በርከት ያሉ ወጣት ኢትዮጵያውን ሰቆቃ እና ችግር ላይ እንደሚገኙ መናገራቸውን ዶቼ ቬለ ዘግቧል። 


ጣቢያው አነጋገርኳቸው ያላቸው በእስር ቤት የታጎሩ እና ግፍ እየተፈፀመብን ነዉ ያሉ ኢትዮጵያዉያን ወጣቶች፤ በመኖርያ ፈቃድ ሰበብ ሴት ኢትዮጵያዉያን ለእስር ተወስደዉ እንደተደፈሩ ተናግረዋል። 


"በካርቱም ከተማ ከመንገድና ከመኖሪያ ቤታቸው ታፍሰው የታሰሩ ኢትዮጵያውያን በጣም በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ናቸው፤ ይገረፋሉ፤ ይደፈራሉ፤ እራሳቸውን ያጠፉ ሁሉ እንዳሉም ተናግረዋል።" 


«ሱዳን ላይ ያለው ችግር በጣም አስከፊ እና አስፈሪ ነው። በተለይ ለኛ ለሀበሾች ሁኔታዉ ከባድ ሆኖብናል፤  በሱዳን አፈሳ ከጀመረ ሁለት ዓመት ሆኖታል፤ ለማን አቤት እንደምንል ግራ ገብቶናል።" ብለዋል። 


"ኤምባሲው ሲጠየቅ ሕጋዊ መሆን አለባችሁ የመኖሪያ ፈቃድ አውጥታችሁ ነው መኖር ያለባችሁ ነው የሚለን። ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ "መፍትሔ ፈልጉልን፣ ለሥራ መውጣት አልቻልንም መንገድ ላይ እየተያዝን ነው።" ሲሉ ተናግረዋል። 


ዶቼ ቬለ ወጣቶቹ ነገሩኝ ብሎ እንደዘገበው "በሱዳን እስርቤት እየታጎረ ያለው ኢትዮጵያዊ እና ኤርትራዊ ነው፤ ለማን አቤት እንደምንል ግራ ገብቶናል፤ ስንቶች እህቶቻችን እና ወንድሞቻችን የት እንደደረሱ አናዉቅም፤ መንግስት በተቻለው መጠን ወደ አገራችን እንዲያስገባን ነው የምንጠይቀው ሌላ ምንም አንፈልግም።» ብለዋል።    


በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በበኩላቸዉ ፤ «በርካታ ኢትዮጵያውያን የመኖሪያ ፈቃድና የስራ ፈቃድ የሌላቸው፤ በሕገ-ወጥ መንገድ የሚኖሩ ናቸዉ።" ብለዋል። አክለውም "ፓስፖርት የሌላቸውን ዜጎቻችን ፓስፖርት የሚያገኙበትን ሁኔታ እያመቻቸን ነዉ፤ የዜጎቻችን መብት ለማስከበርም እየሰራን እንገኛለን።» ነው ያሉት 


በሱዳን ከአንድ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዉያን እንደሚገኙ ይገመታል። 

አስተያየት ይለጥፉ

0 አስተያየቶች