በ Hab HD
ባለፉት ሁለትና ሶስት ዓመታት በጠቅላላው "የለውጥ ኃይል" ነኝ የሚለው ቡድን መንግስታዊ ስልጣኑን ከተቆጣጠረ በኋላ ከመንጋ ፍትህ፤ እስከ ክልሎች ጦርነት፤ ከአፈና እስከ ታዋቂ ሰዎች ግድያ፤ ከድህነት እስከ ዝርፊያ፤ ከስራ አጥነት እስከ መርህ አልባ populistነት (እወደድ ባይነት)፤ ከብሔር እስከ ኃይማኖታዊ ግጭቶች ታዝበናል። ሁሉም ላይ ማለት በሚቻል መልኩ ከመንግስት ቸልተኝነት የተለየ አቋም ነበረን። የመንጋ ፍትህ መቆም አለበት፤ ጦርነት ውስጥ መግባት አይጠበቅብንም፤ ሰዎች በነፃነት ሃሳባቸውን ይግለፁ፤ ግድያ ፍፁም ነውር ነው የሚሉትን ሁሉ አውርተንባቸዋል። ታዲያ 'እነዚህ ሁሉ እያልፈለግናቸው ለምን ቀጠሉ?' ያልን እንደሆን መልሱ አንድ ነው "በቃ!" ስላላልን።
ሃገሪቱና ህዝቦቿ ከፍለን የማንጨርሰው እዳ ውስጥ ተዘፍቀን፤ በየዕለቱ የሚጋሽበው የኑሮ ደረጃ ደሃ ለመባል የማንመጥን እስኪያደርገን በደረስንበት በዚህ ጊዜ መንግስት ሊያደርገው የሚገባው የመጀመሪያ ደረጃ እርምጃው ቅድሚያ የሚሰጠው ሆኖ ሳለ አሁንም ለህዝብ የሚታይ ግልፅ ንቀትና ቸልተኝነት የተሞላበት አካሄድ እየታዘብን ነው። መንግስት በራሱ ተነሳሽነት ሊያደርገው ይገባ የነበረውን መፍትሔ በህዝብ ጥያቄ እንኳን የማያደርግበት ከፍተኛ የንቀት ደረጃ ላይ ያደረሰው አንድ ነገር "በቃ!" አለማለታችን ነው።
ከፍተኛ የህክምና ቁሳቁስና የህክምና ቦታዎች እጥረት፤ እንኳን ጦርነት ተዳምሮበት ብቻውን ከአቅም በላይ የሆነ የመንገድ እና የትምህርት ቤት ችግር፤ ንፁህ የመጠጥ ውሃ እና ሌሎች መሰረታዊ ፍላጎቶች ባልተሟላበት ለመንግስት አሳሳቢ የሆኑት ጉዳዮች ቅድሚያ የሚሰጣቸውም ሌሎች ሆነው እንዲቀጥሉ ያደረጋቸው "በቃ!" አለማለታችን ነው።
እኤአ በ1789 በነበረው የፈረንሳይ አቢዮት በቤተመንግስቷ አቅራቢያ ተቃውሞ በማሰማት ላይ የሚገኙትን የፈረንሳይ ገበሬዎች የዳቦ ጥያቄ ንግስት የነበረችው Marie-Antoinette ከመለሰችበት መንገድ ጋር ተመሳሳይ የሆነ መልስ ለተራበው የኢትዮጵያ ህዝብ እየተሰጠው ይገኛል።
"ምን ሆነው ነው የሚያምፁት"
"ርቧቸው"
"ለምን ኬክ አይበሉም?"
ይሄ ነበር መልሷ።
"ብልህ ከሰው ስህተት ይማራል average የምንለው ከራሱ ስህተት ይማራል በጣም ደደቡ ግን ከሰውም ከራሱም ስህተት አይማርም" እንደሚባለው ቀዳማዊ ኃይለስላሴን፤ ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያምን ወይም የቀድሞውን መንግስት ቸልተኝነት እንደትምህርት መውሰድ ያልቻለው የአሁኑ መንግስታችን ለ"ራበን" ጥያቄያችን
"ኬክ ብሉ"
የሆነውን መልስ እየሰጠን ቀጥሏል ምክንያቱስ? "በቃ!" ስላላልን!
#በቃ_ብንልስ ?
#የዜግነት_ክብር !
0 አስተያየቶች