ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከሽብርተኛ ድርጅትነት በተሰረዘበት የዛሬው የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ልዩ ስብሰባ ላይ 280 የፓርላማ አባላት ተገኝተው ነበር።
ከተገኙት የፓርላማ አባላት መካከል 61 የፓርላማ አባላት ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅትነት መሰረዙን ተቃውመው ድምፅ ሰጥተዋል።
5 የፓርላማ አባላት ድምፀ ተአቅቦ አድርገዋል።
በዚህም በአብላጫ ድምፅ ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅትነት ይነሳ የሚለው የውሳኔ ሃሳብ ፀድቋል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔውን ተከትሎ ባሰራጨው መረጃ ፤ " በህወሓትና በፌደራል መንግስት በኘሪቶሪያ የተደረገውን ሥምምነት ለማጽናት ህወሐትን ከሽብርተኝነት ስያሜ ማንሳት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን የውሳኔ ሃሳቡ በቀረበበት ወቅት ተነስቷል " ብሏል።
0 አስተያየቶች