ትናንት መጋቢት 13 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት 1:30 አካባቢ ወጣት የኔወርቅ አበበ ከምሽት የትምህርት ገበታዋ ከጓደኞቿ ጋር በመመለስ ላይ ሳለች በተለምዶ ሞቢል ተብሎ በሚጠራው ሰፈር በሶስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) በታገዘ ዝርፊያ አማካኝነት የእጅ ስልኳንና ቦርሳዋን ተነጥቃ፣ ወደ አስፓልት በመገፍተሯ እስካሁን ባልታወቀ ተሽከርካሪ ተገጭታ ሕይወቷ አልፏል።
መሰል ድርጊቶች አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች እየተስፋፉ መጥተዋል።
በዚህም የትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ስጋት ላይ መውደቃቸውን አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።
ወጣት የኔወርቅ አበበ በ2014 ዓ.ም ከሐረር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአካውንቲንግና ፋይናንስ በዲፕሎማ ተመርቃ በቅርቡ በሐረር መምህራን ማሠልጠኛ ተቋም ትምህርቷን ለማሻሻል በዲግሪ መማር ከጀመረች 3 ቀናት ብቻ እንደተቆጠሩ በሚያሳዝን ሁኔታ ይህችን ዓለም ተሰናብታለች።
0 አስተያየቶች