Ticker

6/recent/ticker-posts

ጋዜጠኛ አልዓዛር ተረፈ ታሰረ

ጋዜጠኛ አልዓዛር ተረፈ ታሰረ


የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መገናኛ ብዙሃን "አል ዐይን ኒውስ " በዘጋቢነት የሚሰራው ጋዜጠኛ አልዓዛር ተረፈ ዛሬ ሐሙስ ሐምሌ 7 ከሰዓት ሲቪል በለበሱ ጸጥታ ኃይሎች መያዙን ባለቤቱ እና ባልደረባው ተናግረዋል። 


ጋዜጠኛው በጸጥታ አካላት ከተያዘ በኋላ በአዲስ አበባ ላምበረት አካባቢ ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዱን አመልክተዋል። 


አልዓዛርን በታሰረበት ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ የጎበኘው ባልደረባው ዳዊት በጋሻው፤ ጋዜጠኛው የተያዘው ላምበረት መናኸሪያ አካባቢ ከሚገኝ ካፌ እንደሆነ ገልጿል። 


የሲቪል ልብስ የለበሱ ሁለት ግለሰቦች ጋዜጠኛውን መታወቂያ እንዲያሳያቸው እንደጠየቁት እና  " እንፈልግሃለን " ብለው እንደወሰዱት የዓይን እማኞች ነግረውኛል ብሏል። 


ሁለቱ ግለሰቦች አልዓዛርን በያዙበት ወቅት " ለችግኝ ተከላ ጥሩ አመለካከት የለህም፤ ‘ቤተ መንግስት ገብተን፤ በደም የበቀለውን ችግኝ እንነቅላለን’ ብለሃል " በሚል ሲወነጅሉት መሰማታቸውን ጋዜጠኛ ዳዊት ተናግሯል። 


" አል ዓይን ኒውስ " የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መገናኛ ብዙሃን ሲሆን በአማርኛ አገልግሎት ክፍሉ በኩል በተለይ የውጭ ሀገር መረጃዎችን እንዲሁም የሀገር ውስጥ መረጃዎችን በማቅረብ ይታወቃል። 


ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችንና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችን በስፋት በማሰር ስሟ ተደጋግሞ እየተነሳ ነው።

አስተያየት ይለጥፉ

0 አስተያየቶች