Ticker

6/recent/ticker-posts

የዓዲግራት መድኃኒት ፋብሪካ በመውደሙ በኢትዮጵያ የመድኃኒት ዋጋ 40 በመቶ ጨመረ

የዓዲግራት መድኃኒት ፋብሪካ በመውደሙ በኢትዮጵያ የመድኃኒት ዋጋ 40 በመቶ ጨመረ


ባለፉት አራት ወራት በመድኃኒቶችና በሕክምና ግብዓቶች ላይ እስከ 40 በመቶ የሚደርስ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን ሪፖርተር ያነጋገራቸው የመድኃኒት አምራቾች፣ አቅራቢዎችና ተጠቃሚዎች ተናግረዋል። ሙሉ ለሙሉ የተዘጉ አስመጪ ድርጅቶች ስለመኖራቸውም ተጠቅሷል።

 

የኢትዮጵያ መድኃኒት ፋብሪካም ባጋጠመው የግብዓት እጥረት ምክንያት መድኃኒቶችን ለማምረት መቸገሩን አስታውቋል። የፋብሪካው ዋና ሥራ አስፈጻሚ መሐመድ ኑሪ (/) ለፋብሪካው የሚያስፈልጉ 95 በመቶ ግብዓቶች ከውጭ የሚመጡ በመሆናቸው፣ በዚህ ወቅት የተባባሰ የውጭ ምንዛሪ እጥረት በመኖሩ ፋብሪካው 50 በመቶ በታች በሆነ አቅሙ እያመረተ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

 

በኢትዮጵያ መድኃኒት የሚያመርቱ አሥር ፋብሪካዎች ቢኖሩም፣ የአገር ውስጥ ፍላጎትን ለመሸፈን ባለመቻላቸው 90 በመቶ በላይ የሚሆኑት መድኃኒቶች  በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት (የቀድሞ ኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ) አማካይነት ከውጭ እየተገዙ ለመንግሥት ጤና ተቋማት እንደሚሠራጩ መረጃዎች ያሳያሉ።

 

አገልግሎቱ 38% የሚሆነውን የአገር ውስጥ ምርት አቅርቦት የሚሸፍንለት የዓዲግራት መድኃኒት ፋብሪካ በአሁኑ ጊዜ ስለማያመርት፣ እነዚህን ምርቶች ከውጭ ለማስመጣት መገደዱን የኮሙዩኑኬሽን ኃላፊው አቶ አወል ሐሰን ገልጸዋል።

 

የብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ሞኒተሪንግና ሪዘርቭ አስተዳደር ዳይሬክተር / የእኔሐሳብ ታደሰ በበኩላቸው ለመድኃኒትና ለሕክምና ግብዓቶች 15 በመቶ የውጭ ምንዛሪ መፈቀዱን አስታውሰው በመመርያ የተፈቀደውን ያህል ባንኮች ቅድሚያ ሰጥተው እንዲያስተናግዱ ክትትል ይደረጋል ብለዋል። ቅሬታ ያለባቸው አካላት ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ ሲሉም ገልጸዋል።


አስተያየት ይለጥፉ

0 አስተያየቶች