የመስቀል አደባባይ ባለቤትነትን አስመልክቶ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያኖች ዛሬ ሰኞ በመንበረ ፓትሪያሪክ ተገኝተው ተቃውሟቸውን እያሰሙ ይገኛሉ።
የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ምዕመናን አባቶች ለጥያቄዎቻችን መልስ እየሰጡን አይደለም ብለዋል።
የተቃውሞው ምክንያት እሁድ እለት በሐዋርያ ዳንኤል ጌታቸው አማካኝነት በተደረገ ጥሪ መሰረት በመስቀል አደባባይ ሀይማኖታዊ ስርዓት በመከወኑና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ መስቀል አደባባይ በግብር ከፋዮች የተገነባ የሁሉም ንብረት ነው ማለታቸው እንደሆነ ተቃዋሚዎቹ ገልፀዋል።
የቤተክርስቲያን ይዞታ ይከበር፣ አባቶች ከፊት ይምሩን ሲሉም ምእመናኑ ጠይቀዋል።
0 አስተያየቶች