Ticker

6/recent/ticker-posts

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር የስልክ ውይይት አደረጉ

 




ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት  ባይደን ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ግልፅ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን አስታወቁ።

 

ከፕሬዝዳንት  ባይደን ጋር በተለይም በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ  የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ጠቁመዋል።

 በውይይታቸውም የአሜሪካው ፕሬዝደንት  ባይደን በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደረግ፣ በትግራይ ክልል በሚገኙ ያልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደረገው የአየር ጥቃት እንዲቆምና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት የታሰሩ ዜጎች እንዲፈቱ  እንዳሳሰቡ ጽህፈት ቤታቸው ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል፡፡

 

አሜሪካ የኢትዮጵያ መንግሥት  በረሃብና በጦርነት በሰላማዊ ዜጎች ላይ አድርሷል ያለችውን የመብት ጥሰት እንዲያቆም ካስጠነቀቀች በኋላ በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ላይ ከአጎአ (African Growth and Opportunity Act (AGOA)) ተጠቃሚነት አግዳለች፡፡

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ  ትስስር ገፃቸው ላይ እንዳሰፈሩት ውይይቱ  ሁለቱ አገራት በጋራ መከባበር ላይ የተመሰረተ ገንቢ ተሳትፎ በማድረግ ትብብራቸውን ለማጠናከር ትልቅ ጥቅም እንዳለው ሁለታችንም ተስማምተናል ብለዋል።

 

 


አስተያየት ይለጥፉ

0 አስተያየቶች