Ticker

6/recent/ticker-posts

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ኢትዮጵያ ፣ ማሊ እና ጊንን ከAGOA እንዲሰረዙ ፈርመዋል።



ውሳኔው እኤአ ከጥር 1 (ታህሳስ 24 ቀን 2014 . ጀምሮ ተፈፃሚ ይሆናል።


ኢትዮጵያ የተሰረዘችው ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ ተፈፅሟል ለተባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው። 


ከመሰረዟ በፊት የሁለት ወራት የማሰቢያ ጊዜ ገደብ ተሰጥቷት ነበረ። 


ምንም እንኳን ኢትዮጵያ በAGOA ላይ እንድትቆይ  ከፍተኛ ተሰሚነት ያላቸው የኮንግረስ መሪዎች ለፕሬዝደንት ባይደን ደብዳቤ ቢፅፉም እሳቸውን ግን ኢትዮጵያን ከAGOA ሰርዘዋታል።


ኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት ያህል ከቆየችበት የAGOA ተጠቃሚነት እንዳትሰረዝ የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ካውንስል ከፍትኛ ግፊት ሲያደርግ ነበር።


የፕሬዝደንት ጆ ባይደን ውሳኔ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሰራተኞች ሴቶችን ጨምሮ እንዲጎዱ የሚያደርግ ነው።


ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ኢትዮጵያን AGOA ተጠቃሚነት ውጭ ማድረግ፤ ከግጭቱ ጋር ምንም አይነት ግንኙት  የሌላቸውን ከ200 ሺህ  በላይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የበርካታ ሴቶች ኑሮ ላይ ተጽእኖ እንደሚኖረው ማሳወቋ ይታወሳል።


በግብዓት አቅርቦት ሰንሰለት የሚሳተፉትን የ1 ሚሊዮን ሰዎች ህይወት። በእጅጉ እንደሚጎዳው መግለጿ አይዘነጋም።



African Growth and Opportunity Act (AGOA) የግብይት ስርዓት ነው፤ ይህ የግብይት ስርዓት የተወሰኑ የብቃት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ከሳሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት ሸቀጦችን ያለቀረጥ ለአሜሪካ ገበያ እንዲሸጡ የሚፈቅድ ነው።


አስተያየት ይለጥፉ

0 አስተያየቶች