በገዳይነቱ 40 ዓመታትን ያስቆጠረው ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ በአገረ አሜሪካ ቫይረሱን መከላከል የሚያስችል ክትባት እንደተገኘለት ተገልጿል፡፡
‘አፕሪቱድ’ ወይም ‘ካቦቲግራቪየር’ የተሰኘው ይህ ክትባት በተለይም ለቫይረሱ ተጋላጭ ለሆኑ እና ከ35 ኪሎ ግራም በላይ ክብደት ላላቸው ወጣቶች እንዲሰጥ አሜሪካ አጽድቃለች፡፡
ክትባቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ወር ውስጥ ሁለት ጊዜ ለተጋላጭ ወጣቶች ከተሰጠ በኋላ በየሁለት ወሩ እንደሚሰጥ የተገለጸ ሲሆን ይህ ክትባት በተለይም በየእለቱ የእንክብል መድሃኒትን መውሰድ ለማይችሉ ጥሩ መፍትሄ ይሆናል መባሉ ነው የተገለጸው።
ይህ አዲስ ጸረ ኤድስ ክትባት በ13 አገራት ላይ ለቫይረሱ ተጋላጭ ለሆኑ ወጣቶች በሙከራ ደረጃ ተሰጥቶ በእንክብል መልኩ ሲሰጥ ከነበረው ጋር ሲነጻጸር 90 በመቶ ውጤታማ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በዓለማችን በየዓመቱ 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዜጎች በኤችአይቪ ኤድስ ቫይረስ የሚያዙ ሲሆን በ2020 ዓመት ብቻ ከ680 ሺህ በላይ ዜጎች በዚሁ ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
0 አስተያየቶች