Latest

ads header

ዜና

የአማራ ክልል መንግሥት ተማሪዎች በጦርነት ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረበ።

ተማሪዎች በጦርነት ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀረበ።

 

የአማራ ክልል መንግስት ዛሬ (ነሐሴ 24 ቀን 2013 .ም) ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ላይ በሙሉ ጤንነት ላይ የሚገኙ ተማሪዎች በኢትዮጵያ መንግስት መሪነትና በትግራይ ክልል ኃይሎች መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቧል።

 

"የተከፈተብን  ጦርነት የህልውና ነው፡፡" ያለው የክልሉ መንግስት "እድሜያችሁና ጤንነታችሁ  ለደጀንነትም ሆነ ለወታደርነት ብቁ የሆነ የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ የመለስተኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ የመሰናዶና ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ተማሪዎች፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት(የዩኒቨርሲቲ) ተማሪዎች እንዲሁም ምሩቃንና መላው መምህራን በያላችሁበት የክልሉ አካባቢዎች ባለው አደረጃጀት መሰረት "ጠላትን ለመቅበር" እንድትከቱ ጥሪያችንን እናቀርባለን። " ብሏል።

 

አንድ አመት ሊሞላው ሁለት ወራት ብቻ በቀሩትና ሚልዮኖችን ለመፈናቀል፤ በሽህዎች የሚቆጠሩትን  ደግሞ ለህልፈተ ህይወት በዳረገው በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል እየተካሄደ ባለውና ክልሉ "የህልውና ዘመቻ" ባለው ላይ ጦርነት ላይ አካላት ምስጋናውን አቅርቧል።

 

ክልሉ በመግለጫው በሁሉም ደረጃ ላይ ያሉ "ጤናማ" ተማሪዎች የሀገር መከላከያ ሰራዊትንንና ልዩ ኃይልን እንዲቀላቀሉና እንዲያጠናክሩ፤

 

"በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የጀመርነው የህልውና ትግል ሳይደናቀፍ "በአሸናፊነት እንዲቋጭ" የሚጠበቅባችሁን ሁሉ እስከ ህይወት መስዋእትነት ድረስ ሳትሰስቱ እንድታበረክቱ ከአደራ ጋር ጥሪያችንን እናቀርባለን።" ሲል ክልሉ ጥሪ አቅርቧል።

 

በትግራይ ክልል የተጀመረውና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (/) በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ቀርበው እንደተና የኤርትራ ወታደሮች የተሳተፉበት ጦርነት ከትግራይ ክልል አልፎ ወደ አማራና ዓፋር ክልሎችም ተስፋፍቷል።

 

 

 


ምንም አስተያየቶች የሉም