ፖሊስ የጥምቀት በዓልን ለማክበር የሚወጣው ምዕመን አርማ የሌላቸውን ባንዲራ ይዞ መውጣት እንደማይችል ሲያስታውቅ፤ የአማራ ክልል ልዩ ኃይሉን አርማ በሌለው ባንዲራ አስመርቋል
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ምእመኑ ከበዓሉ አላማ ውጭ የሆኑ ድርጊቶችን ከማድረግ ተቆጥቦ የበኩሉን ድርሻ መወጣት አለበት ብለዋል።
በዓሉ በሚከበርባቸው ሁለት ቀናት ወደ ማክበሪያ ቦታው መግባት የሌለባቸው ግጭት የሚቀሰቅሱ ጽሑፎች ፣ አርማ የሌለው ባንዲራ እንዲሁም ስለታማ ነገሮች ይዞ መግባት እንደማይቻልም አጽኖት ሰጥተው ተናግረዋል::
በሌላ በኩል የአማራ ክልል ልዩ ኃይሉን ዛሬ ጥቅምት 9 ቀን 2014 ዓ.ም አርማ በሌለው ባንዲራ አስመርቋል።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ይልቃል ከፋለ(ዶ/ር) ጨምሮ የክልሉ ባለስልጣናት ተገኝተዋል።
0 አስተያየቶች