Ticker

6/recent/ticker-posts

የአማራ ክልል መንግስት የፋኖን ትጥቅ እንደማያስፈታ አስታወቀ::

የአማራ ክልል መንግስት የፋኖን  ትጥቅ እንደማያስፈታ አስታወቀ::


መንግሥት ፋኖን ትጥቅ ሊያስፈታ ነው " እየተባለ ያለው  መሰረት የሌለውና የአማራን ሕዝብ ለመከፋፈል የታለመ ‹‹የጠላት ሴራ ነው›› ሲል የክልሉ መንግሥት አስተባብሏል::

 

" ፋኖ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ሀገርና ሕዝብን እየታደገ ያለ መከታ ኃይል ነው። ስለሆነም የፌደራልም ሆነ የክልል መንግሥት ፋኖን  ትጥቅ የማስፈታት ሐሳብ  የለውም፤ ሊኖረውም አይችልም " ስልም ክልሉ ከፋኖ አባላት ጋር ባደረገው ውይይት ይፋ አድርጓል::

 

በቀጣይ የአማራ ክልል መንግሥት የመሳሪያ አስተዳደር ሥርዓቱን ሊያሻሽል እንደሚችል በውይይት መድረኩ ላይ ተገልጿል።

 

በውይይት መድረኩ  " ፋኖ በስምም ሆነ በግብሩ የአማራ ሕዝብ ክብር መገለጫ በመሆኑ ስሙ የሚነግዱ አካላትን ፋኖና መንግሥት በጋራ ይታገላሉ:: ፋኖን ማደራጀትና ማጠናከር የክልሉ መንግሥት አቅጣጫና ተግባር ሆኖ ሳለ ትጥቅ ማስፈታት የሚለው አሉባልታ አማራን የመከፋፈል እርስ በርስ የማጋጨት የማዳከም ሴራ አካል ነው " ተብሏል::

የፌደራል መንግሥት ሰሞኑን ባወጣውና ለውይይት ባቀረበው ሰነድ ላይ ከመንግሥት ቁጥጥር ውጭ ነው ያለውን ትጥቅ ማስፈታት እንደሚገባ አካትቷል፡፡




አስተያየት ይለጥፉ

0 አስተያየቶች