Ticker

6/recent/ticker-posts

በአፋር ጦርነቱ ለፈጠረው መፈናቀል የሰብዓዊ ድጋፍ ፈተና

ከትግራይ ክልል ጋር ሰፊ የአስተዳደር ወሰን ያለው የአፋር ክልል በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ከተጠቁና ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ ከተከሰተባቸው ነው፡፡ 


በሰሜን የአገሪቱ ክፍል የኢትዮጵያ መንግስትን የሚዋጋው ህወሓት በአፋር በርካታ ስፍራዎችን ከተቆጣጠረበት ከወጣም በኋላ ከሳምንታት በፊት እንዳድስ የማያቋርጥ የከባድ መሳሪያ ተኩስ ከፍቶበታል በተባለው የአፋር ክልል ዞን ሁለት ዋና ከተማ አብዓላ ከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ መከሰቱ ነው የሚነገረው፡፡


ከትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀሌ 40 .. ገደማ ቅርበት ላይ እንደምትገኝ በሚነገረው አብዓላ በዚሁ የቅርብ ጊዜ ግጭት ብቻ 40 ሺህ በላይ የከተማዋ ነዋሪዎች ተፈናቅለው አብዛኞቹ አሁን ላይ በመጠለያ ካምፕ ውስጥ እንደሚገኙ ነው የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ቢሮ ኃላፊ አቶ መሃመድ ሁሴን ለዶይቸ ቬለ የተናገሩት፡፡ 


በሰመራ-አብዓላ-መቀሌ ኮሪደር ወደ ትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፎችን ለማድረስ ብቸኛው መንገድ እንደሆነ የሚነገረው በዚህ የአፋር ዞን 2 አብዓላ ከተማ ላይ ቅጭት የተቀሰቀሰው የፌዴራሉ መንግስት ወታደራዊ ሰራዊቱ ወደ ትግራይ ክልል እንዳይገባ ትዕዛዝ ባስተላለፈበት ማግስት መሆኑን ነው ኃላፊው ሚጠቁሙት፡፡ 


በአፋር በኩል ይህ የእርዳታው ኮሪደር እንዳይዘጋ በዑጋዞችና የአገርሽማግሌዎች ጭምር ከፍተኛ ጥረት መደረጉን የሚያወሱት የክልሉ ሰብዓዊ ድጋፍ አስተባባሪው አቶ መሃመድ፤ ለአብዓላ ግጭት መቀስቀስም ህይሓትን ነው የሚከሱት፡፡ 

 


አስተያየት ይለጥፉ

0 አስተያየቶች