Ticker

6/recent/ticker-posts

የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ጠየቀ



የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት ያሰሯቸዉን ጋጠኞች በሙሉ ባስቸኳይ እንዲፈቱ ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ጠየቀ። ተብሎ የሚጠራዉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ (ሲ ፒ ጄ) እንደሚለዉ የኢትዮጵያ መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከደነገገ ካለፈዉ ጥቅምት ማብቂያ ወዲህ ኢትዮጵያ ዉስጥ 14 ጋዜጠኞች ታስረዋል።

 

ከታሰሩት መካከል ሁለቱ የኢትዮጵያ መንግስት በሚቆጣጠረዉ የኢትዮጵያ ማሰራጪያ ጣቢያ (EBC) የራዲዮ ትግርኛ ቋንቋ አዘጋጆች የነበሩ ናቸዉ።

 

ሌሌቹ ኡቡንቱ ቲቪ የተባለዉ የዩቱዩብ ጣቢያ ዋና አዘጋጅ፣ የተራራ ኔትወርክ ዋና አዘጋጅ፣ የሮሐ ቲቪ ተባባሪ መሥራች፣ ለአሶስየትድ ፕረስ የሚሰራ ቪዲዮ አንሺ፣ አንድ ፎት ግራፍ አንሺ፣ ለመንግስት የሚወግነዉ የፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖሬሽን ሪፖርተር ይገኙበታል።


ዛሬ ሐሙስ ይፋ የተደረገው ሲ ፒ ጄ መግለጫ ላይ ሌሎች 6 ጋዜጠኞቹ መታሰራቸዉን ከዚህ ቀደም መዘገቡ ጠቅሷል።

 


ኮሚቴዉ የጋዜጠኞቹን ስም፣የስራ ልምድ፣ የታሰሩበትን ሁኔታ፣ ጊዜ፣ከቤተሰቦቻቸዉና ወዳጆቻቸዉ የቀረበለትን አቤቱታ፣ ፍርድ ቤት መቅረብ አለመቅረባቸዉን ባካተተዉ ዝርዝር መግለጫ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ያላቸዉን የተለያዩ የመንግስት ባለስልጣናን ማነጋገሩንና ለማነጋገር መጣሩን አስታዉቋል።

 

በከሰሐራ  በታች በሚገኙ ሀገራት CPJ ተጠሪ ሙቶኪ ሙሞ እንደሚሉት የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈዉ ጥቅምት ያወጀዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ ፀጥታ አስከባሪዎች ሰዎችን እንደፈለጉ እንዲያስሩና የሕግ ሒደትን እንዲጥሱ ሰፊ ስልጣን ይሰጣል፤ ተቺ ጋዜጠኞችን ሙሉ በሙሉ ያግዳልም።

 



«የኢትዮጵያ መንግስት በሥራቸዉ ምክንያት የታሰሩ ጋዜጠኞችን በሙሉ እንዲፈታና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የመናገር ነፃነትን ለመጨፍለቅ መጠቀሙን ማቆም አለበት» ይላሉ ሙሞ።  

 


አስተያየት ይለጥፉ

0 አስተያየቶች