በአዲስ አበባ ትናንት በጣለው ዝናብ አንድ ተማሪ በጎርፍ እንደተወሰደ ተነገረ።
ተማሪው በጉለሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ላዛሪስት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርት ቤት ተማሪ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ተማሪው በጎርፍ የተወሰደው በትናንትናው ዕለት ማለትም ረቡዕ 9 ሰዓት አካባቢ በጣለው ዝናብ መሆኑን የአዲስ አባባ እሳትና ድንገተኛ አደጋ የኮሙኒኬሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ ንጋቱ ሙሉ ተናግረዋል፡፡
በጎርፉ የተወሰደው ተማሪ በትምህርት መውጫ ሠዓት ላይ ከትንሽ ወንድሙ ጋር ወደ ቤት እየሄዱ እንደነበርም ተገልጿል፡፡
እስከዛሬ ጠዋት የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ሠራተኞቹ ከኅብረተስቡ ጋር በመሆን ተማሪውን የመፈለጉን ሥራ ቀጥለዋል ተብሏል፡፡
ወላጆች በክረምቱ ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ሲልኩም ሆነ ሲቀበሉ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉላቸው የእሳትና ድንገተኛ አደጋ አሳስቧል፡፡
0 አስተያየቶች