Ticker

6/recent/ticker-posts

በደቡብ ወሎ ተጨማሪ ከ250 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተገለፀ


የዞኑ አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት ሰሞኑን በደቡብ ወሎ ዞን በተቀሰቀሰው ጦርነት ብቻ ከ250 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል ብሏል። 


የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ መሳይ ማሩ ለጀርመን ድምፅ ዶቼቬሌ እንደገለፁት ካለፈው ሳምንት መጀመሪያ ጀምሮ እንደአዲስ በተቀሰቀሰ ጦርነት በደቡብ ወሎ ዞን የተፈናቃይ ቁጥር ከቀን ወደቀን እየጨመረ ነው ብለዋል። 

አቶ መሳይ እንዳሉት ከሆነ እየተፈናቀሉ ያሉት አረጋውያን፣ ሴቶች እና ህፃናት ናቸው ብለዋል። 


ከዚህ ቀደም በደሴ ከተማ 450 ሽህ ተፈናቃዮች እንደነበሩና አሁን የተፈናቃዮች ቁጥር 700 ሽህ መድረሱን አመልክተዋል። 


ኃላፊው እንደገለፁት ተፈናቃዎችን ለማስተናገድ የመጠለያ እጥረት ከፍተኛ ችግር ሆኗል። 

ከዚህ ቀደም 24 ትምህርት ቤቶች ተፈናቃዮችን ይዘው የነበረ ሲሆን አሁን ላይ 45 ትምህርት ቤት ደርሷል። 


ከትምህርት ቤት በተጨማሪ የመንግስትና የግል ሼዶች፣ የተጀመሩ የመንግስት የቢሮ ግንባታዎች ጭምር ለተፈናቃይ መጠለያ እንዲሆን እየተደረጉ መሆኑንም አክለዋል። 


በተለይ መርሳ፣ ድሬ ሩቃ ከሚባሉ አካባቢዎች አጠቃላይ ሊባል በሚችል ደረጃ ህዝቡ አካባቢውን ጥሎ መምጣቱን ገልፀው ፤ ከባቲ እስከ ሀርቡ የመንግስት ትምህርት ቤቶች በተፈናቃዮች ተይዘዋል ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

አስተያየት ይለጥፉ

0 አስተያየቶች