Ticker

6/recent/ticker-posts

ሾልኮ የወጣ ሰነድ አገራት በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ያላቸውን አቋም አጋለጠ

 

Tom Wang / Alamy

ቢቢሲ ሾልኮ ከወጣው ሰነድ አረጋግጫለሁ እንዳለው ሳዑዲ አረቢያ፣ ጃፓን እና አውስትራሊያ የተባበሩት መንግሥታት በካይ ጭስ የሚያመነጩ የኃይል ምንጮች ያላቸውን የጉዳት መጠን አሳንሶ እንዲያቀርብ እየጎተጎቱ ይገኛሉ። 


በተጨማሪም ሰነዱ ሃብታም የሚባሉት አገራት ደሃ ለሚባሉት ወደ አረጓዴ ቴክኖሎጂ እንዲሸጋገሩ የሚያዋጡት ብር እያሳሰባቸው እንደሆነ አሳይቷል። 


ሰነዱ በሚቀጥለው የፈረንጆቹ ወር በሚካሄደው የአየር ንብረት ለውጥ ስብሰባ ላይ ጥላ ያጠላበታል ተብሎ ተሰግቷል። 


በጎን የተባበሩት መንግሥታትን እየጎተጎቱ ያሉ አገራት በሚቀጥለው ወር ተሰባስበው የዓለም የሙቀት መጠን ወደ 1.5 ሴልሺዬስ ለማውረድ ይመክራሉ። 


የሾለከው ሰንድ እንሚያሳየው አገራቱ በመንግሥታት፣ በኩባንያዎችና ያገባናል በሚሉ ድርጅቶች አማካይነት ከ32 ሺህ በላይ ቅሬታዎችን አስገብተዋል። 


በሚቀጥለው ወር ለዓለም የአየር ንብረት ለውጥ "መፍትሔ ለማምጣት" ተሰባስበው የሚመክሩትም እነዚሁ ሀገራት ናቸው። 


የተባበሩት መንግሥታት በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ ያሉ ቅሬታዎችን የሚሰማ ተቋም አለው። ተቋሙ ባለፉት ስድስትና ሰባት ዓመታት የሰበሰባቸውን ቅሬታዎች ይገመግማል። 


ግምገማው መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ምን እርምጃ መወሰድ እንዳለበት ለመወሰንና ከመጥቀም አልፎ ለስብሰባው እንደ ግብዓት ይሆናል።

አስተያየት ይለጥፉ

0 አስተያየቶች