ሩስያ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ጦርነት ያለቅድመ ሁኔታ እንዲቆም ጠየቀች
የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪያ ዛካሮቫ በትዊተር " በ[ኢትዮጵያ]መንግስት እና በሕወሓት ኃይሎች መካከል ያለው ጦርነት እየተባባሰ መምጣቱን እየተመለከትን ነው። የኢትዮጵያን ሁኔታ እየተከታተልን ነው" ብለዋል።
💬#Zakharova: We are monitoring the developments in #Ethiopia as military clashes are intensifying between the government troops and the Tigray People's Liberation Front.
— MFA Russia 🇷🇺 (@mfa_russia) October 21, 2021
☝️ We urge the parties to the conflict to cease fire without preconditions to stabilize the situation. pic.twitter.com/29DoZSNq94
አክለውም " ተፋላሚዎቹ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ጦርነቱን እንዲያቆሙና ሁኔታው እንዲረጋጋ እንጠይቃለን።" ብለዋል።
ሩሲያ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት "የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ነው" በማለት ስትገልፀው ቆይታለች።
ከሩሲያ በተጨማሪ ህንድና ቻይናም ተመሳሳይ አቋማቸውን በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክርቤት ላይ ሲያሰሙ ተደምጠዋል።
ሩሲያ በኢትዮጵያ ላይ ባሳየቺው አቋም በበርካታ በኢትዮጵያውያን በኩል ተወድሳለች።
ባለፈው ሐምሌ ወር ሩሲያና ኢትዮጵያ ወታደራዊ ስምምነት በአዲስ አበባ መፈፀማቸው ይታወሳል።
0 አስተያየቶች