በትግራይ ክልል
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የባንክ ሂሳብ ከፍተው
በጦርነቱ ምክንያት ሂሳባቸው
የታገደባቸው የባንክ ደንበኞች
እገዳው እንደተነሳላቸውና ሂሳባቸውን
ማንቀሳቀስ እንዲችሉ መፈቀዱን
ዋዜማ አስነብባለች።
አንድ ዓመት
ሊሞላው የ10 ቀናት ዕድሜ የቀረው
የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት መጀመሩን ተከትሎ
በትግራይ ክልል ያለው
የባንክ አገልግሎት ሲቋረጥ
በትግራይ ክልል የተከፈቱ
የባንክ ሂሳቦች እንደይንቀሳቀሱ
መታገዳቸው ይታወሳል። ለእገዳው
ምክንያት የነበረው ከፀጥታ
ስጋት ጋር
የተያያዘ የገንዘብ ዝውውርን
መግታት እንደነበር ብሔራዊ ባንክ ገልፆ ነበር።
ዋዜማ አንድ የኢትዮጵያ ንግድ
ባንክ ከፍተኛ
የስራ ሀላፊ
ነገሩኝ ስትል እንዳስነበበቺው ትግራይ ክልል
ሂሳብ የከፈቱ
ደንበኞቹ የታገደባቸውን ሂሳብ
ለማንቀሳቀስ ከፈለጉ አቅራቢያቸው
ባለ የኢትዮጵያ
ንግድ ባንክ
ቅርንጫፍ ቀርበው የታገደባቸውን
ሂሳብ ማንቀሳቀስ
እንዲፈቀድላቸው የሚጠይቅ ማመልከቻ
በመጻፍና ከማመልከቻው ጋርም
ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያን
እንዲሁም የሂሳብ ደብተራቸውን
በማያያዝ ጥያቄያቸውን ማቅረብ
ይችላሉ።
ባንኩም አስፈላጊውን
ማጣሪያ አድርጎ ደንበኞቹ
ሂሳባቸውን እንዲያንቀሳቅሱ ያደርጋል ብለዋል።
ትግራይ ክልል
ተከፍተው በጦርነቱ ሳቢያ
መንቀሳቀስ ያልቻሉ ሂሳቦችን
እንዲንቀሳቀሱ የማድረጉን ስራ
ግን ከኢትዮጵያ
ንግድ ባንክ
ውጭ ሁሉም
የግል ንግድ
ባንኮች ስለመጀመራቸው ማረጋገጥ
አልተቻለም። የአንድ
የግል ንግድ
ባንክ ፕሬዝዳንት
ስለ ጉዳዩ
መረጃ እንደሌላቸውም
ተናግረዋል።
በፌዴራል መንግስትና
በህወሀት መካከል የተነሳውን
ጦርነት ተከትሎ በትግራይ
ክልል ባንኮች
ከአገልግሎት ውጭ መሆናቸው
ብቻ ሳይሆን
በክልሉ ባሉ የሁሉም
ባንኮች ቅርንጫፎች የተከፈቱ
ሂሳቦች መታገዳቸው በርካቶችን
ለችግር ዳርጓል። በትምህርትም ሆነ
በስራ አጋጣሚ
ትግራይ ክልል ኖረው
እዛው የባንክ
ሂሳብ ከከፈቱ
በኋላ መኖርያ
እና መስሪያ
ቦታቸውን የቀየሩ ግለሰቦች
የባንክ ሂሳባቸው መታገዱ
ያላቸውን ገንዘብም ሆነ
የወር ደሞዛቸውን
ሳይቀር ማንቀሳቀስ አቅቷቸው
ተቸግረዋል።
በመሆኑም በርካቶች
ገንዘብን ለማንቀሳቀስ ሌላ
የባንክ ሂሳብ ማውጣትንም
እንደ አማራጭ
ወስደዋል።
የፌዴራል መንግስት
ጦር ክልሉን
ለቆ ከወጣ
በኋላ ክልሉን
በጊዜያዊነት ሲያስተዳድሩ በነበሩ
ሰራተኞች የተጻፉ ቼኮች
እንዳይመነዘሩ ለኢትዮጵያ ንግድ
ባንክ ትእዛዝ
መሰጠቱም ይታወሳል።
0 አስተያየቶች