Latest

ads header

ዜና

ጆ ባይደን በኢትዮጵያ ጉዳይ ትዕዛዝ ፈረሙ



ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለባይደን ግልፅ ደብዳቤ አውጥተዋል

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ግጭትእንዲራዘም ሰበብ በሚሆኑ ተጠያቂዎችና ተባባሪዎቻቸው ላይ አዲስ ማዕቀብ ለመጣል የሚያስችልያሉትን ትዕዛዝ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባይደን ዛሬ ፈርመዋል።

 

ትዕዛዙየኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታትን እንዲሁም ህወሃትንና የአማራ ክልላዊ መንግሥታትን በተጠያቂነት መያዝ እንዲችልለዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር አስፈላጊ ያሉትን ሥልጣን የሚሰጠው እንደሆነ ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል።

 

በሌላ በኩል ፕሬዚዳንት ባይደን ትዕዛዙን ይፋ ካደረጉ በኋላ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ባወጡት ለፕሬዚዳንት ባይደን ይድረስ ባሉት ባለ ሦስት ገፅግልፅ ደብዳቤየዩናይትድ ስቴትስ ተከታታይ አስተዳደሮች በኢትዮጵያ ላይይዘዋቸዋልባሉትየተዛባ አመለካከትቅሬታ አዘል መልዕክት አስተላልፈውኢትዮጵያ ከሚሊዮኖች ደኅንነት ይልቅ ሥልጣንን መጠቅለልን በሚመርጡ የተከፉ ሰዎች የተቀነባበረ ተፅዕኖ ለሚያስከትላቸው መዘዞች አትንበረከክምብለዋል።

 

ከኤርትራ መንግሥትና ከህወሓት እስካሁን የተሰማ ምላሽ የለም።


ምንም አስተያየቶች የሉም