Ticker

6/recent/ticker-posts

የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ወደ መቐለ ተጓዘ



በአፈ ጉባኤ ታገሠ ጫፎ የሚመራ የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ከሁለት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ መቐለ ተጉዟል።


የልኡካን ቡድኑ ወደ መቐለ የተጓዘው የሰላም ስምምነቱን የትግበራ ሂደት ለመቃኘትና በስምምነቱ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች በታቀደው መሠረት እንዲፈጸሙ ለማድረግ መሆኑ ተገልጿል። 


የልኡካን ቡድኑ ከኹለት ዓመት በኋላ ወደ መቐለ የተጓዘ የመጀመሪያው የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ልኡክ ሲሆን፤ ስምምነቱ በመልካም ሁኔታ ላይ  እንደሚገኝ ማሳያ መሆኑ ነው ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገልጿል።


በልዑካን ቡድኑ የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላትም መካተታቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል።

አስተያየት ይለጥፉ

0 አስተያየቶች