የአዲስ ማለዳ ዘገባ እንደሚያሳየው በበርካታ የአማርኛ ፊልሞች ላይ በመሳተፍ የሚታወቀው ወጣቱ ተዋናይ ታሪኩ ብርሃኑ(ባባ) በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ታውቋል።
ላውንደሪ ቦይ፣ 300 ሺ፣ ሹገር ማሚ፣ ፍቅር እና ፌስቡክ፣ ኢንጂነሮቹ፣ ህይወቴ፣ ወደው አይሰርቁ፣ ከቃል በላይ፣ ህይወት እና ሳቅ፣ ሀገርሽ ሀገሬ፣ እዮሪካ፣ ከባድ ሚዛን፣ ወፌ ቆመች፣ ይመችሽ ያአራዳ ልጅ 2፣ በቁም ካፈቀርሽኝ፣ እንደ ቀልድ፣ እርቅ ይሁን፣ አስነኪኝ፣ ሞኙ ያአራዳ ልጅ 4፣ ወቶ አደር፣ አባት ሀገር፣ ወጣት በ97 እና ባሌ ማነቅያ፤ ተዋናይ ታሪኩ ብርሃኑ(ባባ) ከተወነባቸው ፊልሞች ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው።
በተጨማሪም ተዋናይ ታሪኩ የጉዳዬ ፊልም ደራሲና ዳይሬክተር ሲሆን፤ በ2ተኛው ለዛ አዋርድ፣ በ7ተኛው አዲሲ ሙዮዚክ አዋርድ እንዲሁም በ12 ኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል ላይ በምርጥ ተዋናይነት አሸናፊ ነበር።
በሰላሳዎቹ የእድሜ አጋማሽ ላይ የሚገኘው ተዋናይ ታሪኩ ተውልዶ ያደገው አዲስ አበባ ተክለ ሐይማኖት አካባቢ ሲሆን፤ የአንድ ልጅ አባትም ነበረ።
አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ(ባባ) ባደረበት ድንገተኛ ህመም ምክንያት ዛሬ ታሕሳስ 2/2015 ከዚህ አለም በሞት መለየቱን አዲስ ማለዳ ዘግባለች።
0 አስተያየቶች