Ticker

6/recent/ticker-posts

በአፈ ጉባኤ ታገሠ ጫፎ የተመራ ከፍተኛ የልኡካን ቡድን መቐለ ገባ



በአፈ ጉባኤ ታገሠ ጫፎ የተመራ የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ከሁለት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ መቐለ ገብቷል። 


የድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ምስሎች እንደሚያሳዩት ልኡክ ቡድኑ ከክልሉ ባለስልጣናትና ከኃይማኖት አባቶች ጋር ተገናኝቷል። 


የልኡካን ቡድኑ መቐለ የገባው የሰላም ስምምነቱን የትግበራ ሂደት ለመቃኘትና በስምምነቱ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች በታቀደው መሠረት እንዲፈጸሙ ለማድረግ መሆኑ ተገልጿል። 


የልኡካን ቡድኑ ከኹለት ዓመት በኋላ ወደ መቐለ የተጓዘ የመጀመሪያው የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ልኡክ ሲሆን፤ ስምምነቱ በመልካም ሁኔታ ላይ  እንደሚገኝ ማሳያ መሆኑ ነው ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገልጿል። 


በልዑካን ቡድኑ የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላትም መካተታቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል።

አስተያየት ይለጥፉ

0 አስተያየቶች