Ticker

6/recent/ticker-posts

ቢያንስ 20 የሱዳን ወታደሮች በኢትዮጵያ መገደላቸውን የሱዳን ጦር ገለፀ



በሱዳንና በኢትዮጵያ አወዛጋቢ ድንበር ላይ ቢያንስ 20 የሱዳን ወታደሮች መገደላቸውንና ውጥረቱ እየበረታ መምጣቱን የሱዳን ባለሥልጣን ለብሉምበርግ ተናገሩ፡፡

 

አል ራሺድ ዓሊ የተባሉ በሱዳን የገዳሪፍ ግዛት የድንበር ኮሚሽን አባል ለብሉምበርግ በስልክ እንደገለፁት የሱዳን ወታደሮች ለደረሰባቸው ድንገተኛ ጥቃት ምላሽ ለመስጠት አል ፋሻጋ አካባቢ የሚገኘውን አትባራ ወንዝን አቋርጠዋል፡፡

 

አሊ የሱዳን ወታደሮች በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ ስላደረሱት ጥቃት ስለመኖሩ  የሰጡት ምላሽ የለም፡፡

 

የሱዳን ጦር ቅዳሜ ዕለት በፌስቡክ ገፁ ላይ ይፋ እንዳደረገው፤ ‹‹የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላትና የሚሊሻዎች ጥምር አወዛጋቢ በሆነው የአል ፋሻጋ አል ሱግራ በተባለ ቦታ ላይ ስድስት ሱዳናውያን ወታደሮቹ ተገድለዋል፡፡›› ብሎ ነበር፡፡

 

ጦሩ ‹‹ኃይላችን በወሰደው አጻፋዊ እርምጃ በአጥቂዎች ላይ ከባድ የሰውና የቁስ ኪሳራ አስከትሏል፡፡›› ሲል ገልጿል፡፡

የሱዳን ጦር ይህን ይበል እንጂ አደረስኩኝ ባላው አጻፋዊ ጥቃት ስላደረሰው ጉዳት በዝርዝር የገለፀው ነገር የለም፡፡

 

ጉዳዩን በተመለከተ በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የተባለ ነገር የለም፡፡

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ ስለ ጉዳዩ ጥያቄ ቢቀርብላቸውም ምላሽ አልሰጡም፡፡

 

በኢትዮጵያና ሱዳን መካከል ያለው የሻከረ ግንኙነት እየሰፋ መጥቷል፡፡

ሱዳን በአብዬ ግዛት በሰላም ማስከበር ስራ ላይ የነበረው የኢትዮጵያ ሰራዊት ግዛቷን ለቅቆ እንዲወጣ በጠየቀቺው መሰረት ሰላም የኢትዮጵያ አስከባሪ ሰራዊት ከሱዳን መውጣቱ ይታወሳል፡፡

 

በተጨማሪም ሃገሪቱ በኢትዮጵያ የሚገኙት አምባሳደሯን እንደጠራችና ዜጎቷም ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ማዘዟ አይዘነጋም፡፡

 

ሁለቱም ሃገራት በውስጥ ጉዳያቸው ውጥረት ላይ ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያ በፌደራል መንግስትና በትግራይ ኃይሎች መካከል በተፈጠረው አንድ ዓመት ባለፈው ጦርነትና፤ ሱዳን በተደጋጋሚ በተካሄደባት መፈንቅለ መንግስት ግጭት አልተለያቸውም፡፡

 

 

 

አስተያየት ይለጥፉ

0 አስተያየቶች