በህንድ ቴላንጋና ውስጥ ነዋሪ የሆነው ናቪን የተባለው ግለሰብ ሚስቴ የበግ ስጋ አልበሰለም አለችኝ በማለት ቅሬታውን በተደጋጋሚ ለህንድ ፖሊስ አሳውቋል።ሆሊ በዓል የተሰኘውን በዓል ያለዚህ ምግብ ማሳለፍ አልችልም እርሷም ፍቃደኛ አልሆነችም በማለት አስገራሚውን ክስተት ፈጽሟል።
ከበግ ወይም ከፍየል ስጋ የሚዘጋጀው ይህው ምግብ በህንድ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ይወዱታል። የሚዘጋጀው ከፍየል ሥጋ (ወይም አንዳንድ ጊዜ ከበግ ሥጋ) እና አትክል ነው። ግለሰቡ ምግቡ አልተሰራልኝም በሚል አርብ ምሽት በተደጋጋሚ ለፖሊስ በመደወሉ ቅዳሜ ሙሉ ቀን በፖሊስ ጣቢያ ለማሳለፍ ተገዷል።
ኬንያውያን ቢሆኑ በስጋ አይጣሉም እንዲያው የኬንያው ወንድ ለሚያፈቅራት ሴት በስዋሊህ እንዲህ ይላል "ናኩፔንዳ ካማ ኛማ ቾማ" እንደተጠበስ ስጋ እወድሻለሁ ማለት ነው።
ዳጉ ጆርናል
0 አስተያየቶች