በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር እንዳስታወቀው በከተማዋ የባጃጅና ሌሎች ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ላልተወሰነ ጊዜ ተቋርጧል።
የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ለጊዜው እንዲቋረጥ የተደረገበት ምክንያት በከተማው ያለውን የሰዎች እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ነው ተብሏል።
"የከተማው ወጣቶችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ከጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር በየአካባቢው 'ሰርጎ ገቦችን' በመከታተልና የአካባቢያቸውን ሰላም በማስጠበቅ ሃገራዊ ኃላፊነታቸውን እዲወጡ።" ሲል ከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።
ባለፈው ዓመት በፌደራል እና በትግራይ ክልል መንግሥት መከካል የተፈጠረው ጦርነት ምክንያት በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ለረሃብና ለመፈናቀል ሲዳረጉ፤ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል።
"ሕግ የማስከበር ዘመቻ" በትግራይ የተጀመረው ጦርነቱ አድማሱን በማስፋት "የህልውና ዘመቻ" በሚል ወደ በአማራ ና ዓፋር ክልሎች ደርሷል።
በጦርነቱ ምክንያትም በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል።
በትግራይ ክልል መንግሥ የሚመራውና "የትግራይ መከላከያ ሰራዊት" በሚል ስያሜ የሚጠራው ኃይል ትቅዳሜ እለት የፌደራል ወታደር ኃይሎችን በመግፋት ደሴን ተቆጣጥሬአለሁ ሲል፤ ኃይሉን "አሸባሪ" በሚል የሚጠራው የፌዴራሉ መንግሥት በበኩሉ "ደሴ ከተማ በቁጥጥሬ ስር ናት።" ማለቱ አይዘነጋም።
0 አስተያየቶች