ከሰሞኑ የታሰሩ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ቁጥር ከ16 በላይ ሆነ
በኢትዮጵያ በሁለት ሳምንት ውስጥ በፀጥታ ኃይሎች ተይዘው የታሰሩ ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ቁጥር ከአስራ ስድስት ባላይ መድረሱ ተነገረ።
ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 20/2014 ዓ.ም ጠዋት በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋሏ የተነገረውን ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድን እንዲሁም ትናንት ሁለት ጋዜጠኞች ተይዘዋል።
በዚህም ባለፉት ቀናት ከሥራ ቦታቸውና ከመኖሪያቸው መያዛቸው ከተዘገበው ጋዜጠኞች በተጨማሪ ትናንት አርብ ግንቦት 19/2014 ዓ.ም የፊንፊኔ ኢንተግሬትድ ብሮድካስቲንግ (ኤፍአይቢ) ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ሰቦንቱ አሕመድ እና አልፋ የተሰኘው የዩቲዩብ ገፅ ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው መታሰራቸው ተነግሯል።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አርብ ባወጣው መግለጫመሠረት፣ በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር የዋሉ ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ቁጥር 16 ደርሷል ብሎ የነበረ ሲሆን፣ ቅዳሜ ዕለት ቁጥሩ ወደ 18 ከፍ ማለቱን ገልጿል።
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ “የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ላይ የመተፈፀመው እስርበተለይ አሳሳቢ የሚሆንበት ምክንያት ከሚዲያ ሕግ በተቃራኒ መሆኑ ሳይሆን የሚያስከትለው ውጤት ከመገናኛ ብዙኃንና ሐሳብን በነጻነት ከመግለጽ ባሻገር ስለሚሰፋ ነው” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
ኮሚሽነሩ ጨምረውም ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሚፈፀም እስር እንዲሁም ተጠርጣሪዎች ከታሰሩ በኋላ የት እንደሚገኙ በይፍ አለማሳወቅ መበራከቱን ተችተዋል።
የሚዲያ ሕግን የሚጠሰውን እና ነገሮችን የሚያባብሰውን እስር ተችተው፣ ሁሉም ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በአፋጣኝ እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።
ዋና ኮሚሽነሩ በተጨማሪም “በመገናኛ ብዙኃን አማካይነት ተፈፅመዋል የተባሉት ወንጀሎች ምንም ይሁኑ ምንም፣ አዲስ የተረቀቀውን የሚዲያ ሕግ ለመጻረር ሰበብ መሆን አይገባቸውም። ሕጉ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሰርን በግልጽ ይከለክላል” ብለዋል።
እስካሁን ባለው መረጃ በፀጥታ ኃይሎች ተይዘው በእስር ላይከሚገኙና ፍርድቤት ከቀረቡት መካከል የሚከተሉት ይገኙባቸዋል።
ከአማራ ክልል ባሕር ዳር ከአንድ ሳምንት በፊት በቁጥጥር ሥር የዋሉት የአሻራ ሚዲያ ባልደረቦች ጋሻዬ ንጉሤ፣ ጌትነትያለው፣ ሀብታሙ መለሰ፣ ዳንኤል መስፍን፣ ቀለሙ ገላጋይ ሲሆኑ፣ በተመሳሳይ ከዚያው ከተማ ስማቸው ያልተጠቀሰ አራት ንስር የተባለ የሚዲያ ተቋም ባለሙያዎች ታስረዋል።
በተጨማሪም አዲስ አበባ ውስጥ ከኢትዮ ንቃት ሚዲያ መስከረም አበራ፣ ከገበያኑ ሚዲያ ሰሎሞን ሹምዬ፣ ከፍትሕ መጽሔት ተመስገንደሳለኝ፣ ከኢትዮ ፎረምያየሰው ሽመልስ፣ ከአልፋ ቲቪ በቃሉ አላምረው እናከፊንፊኔ ብሮድካስቱኢንግ ሰቦንቱ አሕመድ ናቸው።
የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ሲፒጄ፣ ከፌደራል ፖሊስ ቃል አቀባይ ጋር ባደረገው የስልክ ንግግር፣ “ከሙያቸው ጋር በተያያዘ የታሰሩ ጋዜጠኞች የሉም” የሚል ምላሽ እንደተሰጠው አስታውቋል።
ጋዜጠኞቹ እንዲሁም የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎቹ “ፖሊስ ወንጀል ስለመፈፀማቸው መረጃ ስላለው” በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ ቃል አቀባዩ እንደተናገሩም ሲፒጄ አክሏል።
ያየሰው ሽመልስ እና ተመስገን ደሳለኝ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ስለቀረበ ቃል አቀባዩ ተጨማሪ መረጃ ከመስጠት መቆጠባቸውንም የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ አሳውቋል።
ስለ ጉዳዩ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ወደ መንግሥት ቃል አቀባዮቹ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ እና አቶ ከበደ ዴቢሳ ስልክ በመደወል እንዲሁም አጭር የጽሑፍ መልዕክት በመላክ ያደረገው ጥረት እንዳልተሳካም ጨምሮ ገልጿል።
የአማራ ክልል “ሕግ የማስከበር” ያለውን ዘመቻ ከጀመረ ወዲህ ማኅበረሰብ አንቂዎች፣ ጋዜጠኞችና በሌሎችም ሙያዎች የተሰማሩ ሰዎች ላለፉት ሳምንታት መታሰራቸው ሲዘገብ ቆይቷል።
ክልሉ ባለፈው ሳምንት በዚህ ዘመቻ ከ4500 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ሥር እንዳዋለ መግለጹም ይታወሳል።
ኢሰመኮ እና ሲፒጄ ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጭ ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች መታሰራቸውን ከመኮነናቸው ባሻገር፣ አሜሪካም የማኅበረሰብ አንቂዎችና የጋዜጠኞች የጅምላ እስር ያሳስበኛል ስትል አዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲ በኩል መግለጫ አውጥታለች።
የፌደራል እና የክልል ፀጥታ አስከባሪ ኃይሎች ሕጋዊ አሠራሮችን መከተል እንዳለባቸው የመብት ተሟጋች ድርጅቶቹና ኤምባሲው ባወጧቸው መግለጫዎች ላይ ተጠቁሟል።
0 አስተያየቶች