ዶ/ር ይልቃል ከፋለ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሆነው ተሸሙ
የክልሉ ምከር ቤት አዲስ አፈ ጉባዔ እና ምክትል አፈ ጉባዔም ሰይሟል።
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት መስረታ በዛሬው እለት እየተካሄደ ይገኛል።
ምክር ቤቱ ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋዬ አለሙ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ፣ አቶ አማረ ሰጤ ምክትል አፈ ጉባዔ አድርጎ ሾሟል።
በተጨማሪም የአማራ ክልል ምክር ቤት ዶ/ር ይልቃል ከፋለን የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል።
ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በተለያዩ ትምህርት ኮሌጆች በመምህርነት፣ ዲን በመሆንና በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንትና ፕሬዝዳንት በመሆን ውጤታማ ኃላፊነትን የተወጡ አመራር መሆናቸው ተገልጿል።
ምንም አስተያየቶች የሉም