የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን አቋርጠዉ የወጡ 12 ሺሕ 993 ተማሪዎች በድጋሚ ፈተናዉን እንደማይወስዱ ትምህርት ሚኒስቴር በድጋሚ አስታወቀ፡፡
የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ጋር በተያያዘ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡
ሚንስትሩ በዚሁ መግለጫቸዉ ላይ በፈተናዉ ሂደት በአጠቃላይ 12 ሺሕ 993 ተማሪዎች ፈተናዉን አቋርጠዉ መውጣታቸውን ገልጸው፤ ትምህርት ሚኒስቴር እነዚህን ተማሪዎች የመፈተን እቅድ እንደሌለዉ መናገራቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል፡፡
ነገር ግን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረዉ የድልድይ መደርመስ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸዉና በፈተናዉ ወቅት የወለዱ ተማሪዎች ከአንድ ወር በኋላ ፈተናዉን እንደሚወስዱ ሚንስትሩ ገልጸዋል፡፡
ለፈተናዉ ዝግጁ ከነበሩ አጠቃላይ ተማሪዎች 98 በመቶ የሚሆኑት ፈተናዉን በአግባቡ መዉሰዳቸዉን የተናገሩት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፤ በየትኛዉም ዩኒቨርሲቲ አንድም የትምህርት አይነት እንዳልተሰረቀ አረጋግጠዋል፡፡
0 አስተያየቶች