Ticker

6/recent/ticker-posts

የደሴና ኮምቦልቻ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን እንዲጠብቁ ከተማ አስተዳደሮቹ አሳሰቡ


     

For daily News Visite Agelgl Media  


ነዋሪዎች በሚነዙ "ሀሰተኛ"  መረጃዎች አትደናገሩ ያለው አስተዳደሩ ማንኛውም የተለየና አጠራጣሪ ነገር ሲመለከቱ ለጸጥታ ኃይል በማሳወቅ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠይቋል።


ከተለያዩ አከባቢዎች ለመጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ነገር ግን በዚህም መሃል ሰርገው ሊገቡ የሚችሉ የጥፋት ኃይሎች ካሉ በመከታተል ለሚመለከተው የጸጥታ ኃይል መጠቆም እንደሚገባ አስተዳደሩ ገልጿል።


የባንክና መሰረታዊ አገልግሎቶች ክፍት ሆነው እየተሰጡ መቀጠል እንዳለባቸውና አገልግሎት በሚያቋርጡና ዋጋ አላግባብ በሚጨምሩ ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወሰድ ማስጠንቀቂያ ተላልፏል።


በከተማው የታወጀውን አሰገዳጅ ህግ ሁሉም ሊያከብረው የሚገባ ሲሆን ጥሰት የሚታይ ከሆነ አስተዳደሩ ትእግስት እንደማያደርግና እርምጃ እንደሚወስድ አጥብቆ አስጠንቅቋል።


የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ "በየመዝናኛ ቤቶችና ህዝብ በሚሰበሰብበት ቦታዎች ላይ አሉባልታ ወሬ በማናፈስ ህብረተሰቡ እንዳይረጋጋ በማድረግ ኗሪው በፍርሃት ከተማውን ለቆ እንዲወጣ ተልዕኮ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች አሉ።" ሲል ገልጿል።


ህብረተሰቡ ይህንን በማወቅ "በአሉባልታ ወሬ" ሳይደናገር የራሱን ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክት አስተላልፏል።


የከተማው ጸጥታ ማዋቅር የከተማውን ሰላም ለማስጠበቅ እየሰራ መሆኑንም የገለፀ ሲሆን ህብረተሰቡ ተደራጅቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርቧል።

አስተያየት ይለጥፉ

0 አስተያየቶች