Ticker

6/recent/ticker-posts

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሃፊ አሚና መሐመድ በትግራይ ጉብኝት አደረጉ

 

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሃፊ አሚና መሐመድ በትግራይ ጉብኝት

በምክትል ዋና ፀሐፊዋ አሚና መሐመድ የተመራ የድርጅቱ የልኡካን ቡድን በመቐለ ከተማ በዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል እና 70 ካሬ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ተዘዋውሮ ተመልክቷል።

 

የድርጅቱ የልኡካን ቡድን የዋና ጸሃፊው የአፍሪካ ጉዳይ ልዩ አማካሪ ክሪስቲና ዱርቴ እና የድርጅቱ ኤጄንሲዎች  ሃላፊዎች የተገኙበት ነው።

በዓይደር ሆስፒታል ባደረጉት ጉብኝት የመድሃኒት እጥረት እና የህክምና ቁሳቁስ መኖሩን ተመልክተዋል፡፡ ለህክምና አገልግሎት የሚውል የእጅ ጓንት እየታጠበ ተደጋግሞ ጥቅም ላይ ሲውል ተመልክተዋል ተብሏል።

 

የመቐለ ከተማ 70 ካሬ የጋራ መኖርያ መንደር አከባቢ ያለውን የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የጎበኘው የልኡካን ቡድኑ ስደተኞቹ ያሉበት ሁኔታ እና ጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ተመልክቷል።

 

የተመድ ኤጄንሲዎች በትግራይ ያለውን ችግር በሪፖርት ደረጃ የሚያውቁት ቢሆንም ምክትል ዋና ጸሃፊዋ በአካል ተገኝተው መጎብኘታቸው አለም አቀፉ ማህበረሰብ ችግሩን ይበልጥ እንዲረዳው እንደሚያግዝ የትግራይ እርሻ እና ገጠር ልማት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር አትንኩት መዝገበ ተናግረዋል።

አስተያየት ይለጥፉ

0 አስተያየቶች