Ticker

6/recent/ticker-posts

ሕወሓት ከመንግሥት ጋር እንደማይደራደር ገለፀ



ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ(ሕወሓት) ከፌደራል መንግሥት ጋር የምደራደርበት ጊዜ አብቅቷል ሲል ገልጿል። 

ፓርቲው ከዚህ ቀደም ሁሉን አካታች ድርድር እንዲደረግ እሻለሁ ሲል ቢቆይም አሁን ግን "የድርድር ጊዜው አብቅቷል።" ብሏል።

በሕወሓት የሚመራውና የትግራይ መከላከያ ሰራዊት(የትግራይ ሰራዊት) የሚል ስያሜ የተሰጠው ኃይል  ዋና አዛዥ ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ በትግራይ ቴሌቪዥን ሲናገሩ "ተደጋጋሚ የውይይትና ድርድር ጥሪዎቻችን አብይ አልተቀበላቸውም ፤ ከዚህ በኋላ ድርድር የሚለው አይሰራም፣ ጦርነቱ'ኮ አልቋል ፤ ከማን ጋር ነው የምንደራደረው?" ብለዋል። 


ዋና አዛዡ አክለውም "አብይ ሀገርና ህዝብ ለዚህ ሁሉ 'እልቂት የዳረገ'፣ ሀገሪቷን ወደ አረንቋ የከተተ 'ደም የጠማው ወንጀለኛ ነው'።" ሲሉ ኮንነዋል። 


የሰላማዊ ድርድሩ በር ዘግተውታል ያሉት ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ድርጊቱን በጦር እናጠናቅቀዋለን ብለዋል።


ከጄኔራሉ ንግግር ጋር ተያይዞ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በመንግሥት በኩል የተባለ ነገር ባይኖርም፤ መንግሥት "አሸባሪ" ሲል ከፈረጀው ሕወሓት ጋር እንደማይደራደር መግለፁ አይዘነጋም። 


የትግራይ ኃይሎች ደሴንና ኮምቦልቻን እንደተቆጣጠሩ መዘገቡ ይታወሳል። 

የጦር አጋራቸው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በበኩሉ ከሚሴን እንደተቆጣጠረ ገልጿል። 


አንድ አመት ያስቆጠረው ይህው ጦርነት በሚልዮን የሚቆጠሩትን ለረሀብና መፈናቀል ሲዳርግ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ሰዎችም ተገድለዋል።

አስተያየት ይለጥፉ

0 አስተያየቶች