መንግሥት በተመድ ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ አብራራ
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሐሙስ እለት በ72 ሰዓታት ውስጥ ሀገር ለቀው እንዲወጡ 7ቱ የተመድ ሰራተኞች ላይ የተወሰነውን እርምጃ አስመልክቶ ማብራሪያ አውጥቷል።
ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማብራሪያው እንደጠቀሰው ኢትዮጵያ ከውሳኔው ላይ ልትደርስ የቻለችበትን ምክንያት ፣ ግለሰቦቹ ሲሳተፉበት ነበር የተባለው "ህገወጥ ድርጊቶች" ያለችውን በዝርዝር አስቀምጧል።
ውጭ ጉዳይ ከዘረዘራቸውና "ህገ ወጥ ድርጊቶች" ካላቸው መካከል፤ ለተቸገረው ህዝብ ተብሎ የሚገባዉን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ዕርዳታ ለTPLF[ሕወሓት] አሳልፎ መስጠት፣ ከመንግስት ጋር የተደረገን ስምምነት መጣስ፣ የመገናኛ መሳሪዎችን TPLF[ሕወሓት] እንዲጠቀምበት ማስተላለፍ፣
ለሰብዓዊ ደጋፍ የሚውሉ ቁሳቁሶችን ይዘው ወደ ትግራይ የገቡና ሳይመለሱ የቀሩ ተሽከርካሪዎች በTPLF [ሕወሓት] ቁጥጥር ስር መዋላቸውንና ለወታደራዊ ተግባር "መዋላቸውን እያወቁ" እንዲመለሱላቸው ለመጠየቅ ተደጋጋሚ "ቸልተኝነት" ማሳየታቸው፣ እንዲሁም "ሀሰተኛና የተዛቡ መረጃዎችን ማሰራጨታቸውና" ሰብዓዊ ድጋፍን ለፖለቲካ ዓላማ እንዲውል ማድረጋቸው የሚሉት ናቸው።
ምንም አስተያየቶች የሉም