Ticker

6/recent/ticker-posts

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ተጨማሪ ከ13 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቀሉ



በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ13 ሺህ በላይ ተጨማሪ ሰዎች መፈናቀላቸውን የክልሉ የአደጋ መከላከልና ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።


ዶቼቬሌ ኮሚሽኑን ጠቅሶ እንደዘገበው በካማሺ ዞን ከሚገኙ ሁለት ወረዳዎች የተፈናቀሉት እነዚሁ ሰዎች ሊቲና ኦዳ በተባሉት አካባቢዎች ተጠልለዋል።


ኮሚሽኑ እንዳለው ለተፈናቃዮቹ ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ ጥረት እየተደረገ ነው። 


በየጊዜው ግጭት በሚነሳበት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ ተቀፈናቃዮች ቁጥር ከ490 ሺህ በላይ ደርሷል።

አስተያየት ይለጥፉ

0 አስተያየቶች