መንግሥት ስድስት ሺህ የሚጠጉ የትግራይ ኃይል ታጣቂዎችን መግደሉ ገለፀ።
የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል እተደረገ ባለው ጦርነት ከ5 ሺህ 600 በላይ የትግራይ ታጣቂ ኃይሎችን ገድያለሁ ብሏል።
ይህን የተናገሩት የመከላከያ ሚኒስቴር የሰራዊት ግንባታ ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ ቅዳሜ እለት በሰጡት መግለጫ ነው።
ሌተናል ጀነራሉ በመግለጫቸው "ጁንታ" ሲሉ የጠሩት የትግራይ ታጣቂ ኃይሎች ተገድለዋል ያሉት በአማራና ዓፋር ክልሎች በሚገኝባቸው የተለያዩ አካባቢዎች ነው።
ባጫ ይህን ይበሉ እንጂ የሞቱት ተዋጊዎች መቼ እንደሆነ ጊዜውን አልጠቀሱም።
ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ ከሁለት ወራት በፊት የትግራይ ኃይሎች ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል ብለው ነበር።
የትግራይ ኃይሎች በበኩላቸው በነሐሴ ወር በተለያዩ የውጊያ ቦታዎች ድል እንዳደረጉ በተደጋጋሚ ሲገልፁ ቆይተዋል።
ከሁለት ወራት በኋላ አንድ አመት የሚሞላው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት የሀገሪቱን ምጣኔ ኃብት እንዲያሽቆለቁል እንዳደረገው ዓለማቀፍ ተቋማት ገልፀዋል።
ምንም አስተያየቶች የሉም