ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በበርሊን ማራቶን በሁለቱም ጾታዎች በአሸናፊነት አጠናቀቁ።
በሴቶች በተካሔደው ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ በመያዝ የበላይ ሆነዋል። ኢትዮጵያዊቷ ጎተይቶም ገብረስላሴ ውድድሩን በ2 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ከ09 ሰከንድ በማጠናቀቅ አንደኛ ወጥታለች። ሕይወት ገብረኪዳን በ2 ሰዓት ከ21 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ ሁለተኛ ስትወጣ ሌላዋ ኢትዮጵያዊት ሔለን ቶላ በ2 ሰዓት ከ23 ደቂቃ ከ05 ሰከንድ በሶስተኛነት አጠናቃለች።
ዛሬ እሁድ በጀርመን ዋና ከተማ በርሊን በወንዶች በተካሔደው የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው ጉዬ አዶላ አሸናፊ ሆኗል። ቀነኒሳ በቀለ ውድድሩን በሶስተኛነት አጠናቋል። ጉዬ 42.2 ኪሎ ሜትር ከሚረዝመው የሩጫ ውድድር ሰባት ኪሎ ሜትር ገደማ ሲቀር ቀድሞ ሔዷል። የ30 አመቱ ጉዬ ውድድሩን በ2 ሰዓት ከ05 ደቂቃ ከ45 ሰከንድ አጠናቋል። ኬንያዊው ቤትዌል ዬጎን ሁለተኛ በመሆን የበርሊን ማራቶን ውድድርን ጨርሷል። ከዘጠኝ ወራት በፊት በኮቪድ-19 ተይዞ ያገገመው ቀነኒሳ በቀለ ውድድሩን በሶስተኛነት አጠናቋል።

ምንም አስተያየቶች የሉም