ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለደመራ በዓል የተላለፈ መልዕክት
በዓሉን ለማክበር ወደ መስቀል አደባባይ ሲኬድ የፀጥታ አካላት በየቦታው ፍተሻ ያደርጋሉ፤ ይህንንም ህዝበ ክርስትያኑ እንዲገነዘብ ተብሏል። ምናልባት ፍተሻው 2 እና 3 ቦታ ቢሆን እንኳን ፍተሻው ለራስ ደህንነት መሆኑን በመገንዘብ ህዝበ ክርስትያኑ ሳይሰላች ለፍተሻው እንዲተባበር ጥሪ ቀርቧል።
ከባንዲራ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ - ወደበዓሉ ቦታ በሚኬድበት ጊዜ ፣ የወጣት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አባላት እንዲሁም ሌሎች አካላት በሀገሪቱ ህገመንግስት የፀደቀውን የፌዴራል አርማ ያለበትን ባንዲራ ብቻ መጠቀም ይገባል ተብሏል፤ አላስፈላጊ ሎጎዎችን እና ህጋዊ ከሆነው ባንዲራ ውጪ መጠቀም አይቻልም፤ ለዚህም ለፀጥታ አካላት ትብብር ማድረግ ያስፈልጋል።
ከኢትዮጵያ ብሄራዊው ባንዲራ ውጪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የምትጠቀምበት «ነዋ ወንጌለ መንግሥት» የሚል አርማ ያለበትን ባንዲራ መጠቀም ይቻላል፤ ህዝበ ክርስቲያኑ ይህንን ባንዲራ ሲጠቀም በስነስርስአቱ የታተመ፣ በሁለቱም በኩል ሎጎው እንዳለ የሚያሳይ መሆን አለበት።
ህዝበ ክርስቲያኑ በዓሉን ለማክበር ወደ መስቀል አደባባይ ሲሄድ የኮቪድ-19 መከላከያ ጥንቃቄዎችን መፈፀም እንዳለበት አደራ ተብሏል። ማስክ ያድርጉ፣ ሳኒታይዘር ያዙ ፤ ርቀታችሁንም ጠብቁ።
የጤና ሚኒስቴር በመስቀል አደባባይ የኮቪድ-19 የክትባት መርሃ ግብር አዘጋጅቷል፤ በቦታው ላይ ክትባት ስለሚሰጥ ቀደም ብሎ በመገኘት የክትባቱ ስነሥርዓት ተሳታፊ መሆን እንደሚቻል ተገልጿል።
ከመስቀል አደባባይ ውጭ የሚደረጉ የመስቀል ደመራ ስነስርዓቶች የፀጥታ ኃይሎችን በመተባበር እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል።
ለበዓሉ ድምቀት በሚል ርችት መተኮስ አይፈቀድም ተብሏል።
Post Comment
ምንም አስተያየቶች የሉም