Ticker

6/recent/ticker-posts

በሽረ በተፈጸመ የአየር ጥቃት የእርዳታ ሰራተኛን ጨምሮ ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ

 

 


በትግራይ ክልል ሽረ ከተማ ላይ በተፈጸመ የአየር ጥቃት አንድ የረድዔት ሰራተኛው መገደላቸውን ዓለም አቀፉ የነፍስ አድን ቡድን (ኢንተርናሽናል ሬስኪው ኮሚቴ) ገለጸ።


Three people including aid worker killed in air strike in Ethiopia's Shire, IRC says


ተቋሙ በዚህ የአየር ጥቃት የረድዔትሰራተኛውን ጨምሮ ሶስት ሰዎች መገደላቸውንም ቅዳሜ ጥቅምት 5 2015 . ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

 

የጤናና የስነ ምግብ ቡድን አባል የሆኑት የረድኤት ሰራተኛው ለሴቶች እና ህጻናት እርዳታ እያቀረቡ ባለበት ወቅት በተፈጸመ ጥቃት ከቆሰሉ በኋላ ህይወታቸው አርብ ጥቅምት 4 2015 . እለት ማለፉን መግለጫው አትቷል።

 

በዚህ ጥቃት ሌላ የአይአርሲ የረድዔት ሰራተኛ የቆሰሉ ሲሆን፣ ሌሎች ሁለት ሰላማዊ ሰዎች እንደተገደሉና እንደቆሰሉ መግለጫው አክሏል።

 

ተቋሙየእርዳታ ሰራተኞች እና ሰላማዊ ዜጎች በፍፁም ኢላማ መሆን የለባቸውምብሏል።

 

የኢትዮጵያ መንግሥት ሽረ ከተማ ላይ ተፈጸመ በተባለው የአየር ጥቃት ላይ ምንም አይነት አስተያየት ባይሰጥም ከዚህ ቀደም ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ እንደማያደርግ መግለጹ ይታወሳል።

 

በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ባሉባት ሽረና አካባቢው ባሉ በርካታ ግንባሮች ጦርነቱ እየተጠናከረ መምጣቱንም ተከትሎ አለም አቀፍ ተቋማት ጦርነቱ እንዲቆም ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።

 

የትግራይ ኃይሎች ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ጦርና የኤርትራ ጦር በከተማዋ እና አካባቢው የከባድ መሳሪያ ድብደባና የአየር ጥቃት እየፈጸሙ ነው ሲሉ ከሰዋል።

 

ይህንንም ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት ሰላማዊ ዜጎች ኢላማ መደረጋቸውን አውግዟል።

 

የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ እና የደህንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ ጆሴፍ ቦረል  በሽረ የቀጠለው ጦርነት እንዲሁም ሰላማዊ ነዋሪዎች ኢላማ የመደረጋቸው ሪፖርት አስደንጋጭ ነውብለዋል

 

"እውነተኛ የሰላም ጥረቶች ወታደራዊ ጥቃቶች ወይም ትንኮሳዎቸ እንዳልሆኑ" በገለጹበት የትዊተር መልዕክታቸው "አለም አቀፉን ህግ ማክበር የሁሉም ግዴታ ነው" ብለዋል።

 

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጦርነቱ መባባሱን በማስመልከት የተፈጠረባቸው "ከባድ ስጋት" ከገለጹ በኋላ ጦርነቱ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

 

"በሽረ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት የፈጸሙት የዘፈቀደ ጥቃት አሳሳቢ ነው"  በማለት የአሜሪካ መንግሥት የተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤይድ) ኃላፊ ሰማንታ ፓወር ተናግረዋል።

 

በተለይም "የኤርትራ ኃይሎች በቅርቡ የሰላማዊ ነዋሪዎች ማዕከላትን ሊቆጣጠሩ እንደሚችሉ የሚገልጹ ዘገባዎች ስጋት እንዳጫረባቸው" ጥቅምት5 2015 ባወጡት የትዊተር መልዕክት ገልጸው "ሰላማዊ ዜጎችን ለመጠበቅ ይህ ጥቃት መቆም አለበት" ብለዋል።

 

ጦርነቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን ከቀያቸው ያፈናቀለ ሲሆን "እነዚህ የተፈናቃዮች መጠለያ ካምፖችም ጥቃት ደርሶባቸዋል" ብለዋል።

 

 "በነዚህ ጥቃቶች የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይልና የኤርትራ መከላከያ ኃይል የተፈናቃዮች መጠለያ ካምፖችን ከተቆጣጠሩ በሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ ተጨማሪ ጥቃት እና ግድያ የመፈጸም እድሉ ከፍተኛ ነው" ብለዋል።

 

አንድ ሚሊዮን የሚደርስ ህዝብ በረሃብ አፋፍ ላይ ባለበት ሁኔታ ሁሉም ወገኖች ከግጭት እንዲታቀቡ ጠይቀዋል።

 

ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የኤርትራ መንግሥት፣ የትግራይ መከላከያ ሰራዊት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደርሱምጥሪያቸውን አቅርበዋል።

 

ሰማንታ ፓወር  በተጨማሪ ዘላቂና ያልተደናቀፈ ሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስና የኤርትራ መከላከያ ሰራዊትም ከኢትዮጵያ እንዲወጣ ጠይቀዋል።

 

በተደጋጋሚ ጦሯ ከኢትዮጵያ እንዲወጣ የተጠየቀችው ኤርትራ በበኩሏ የአውሮፓ ህብረት በትግራይ ጦርነት አጥፊ ሚና እየተጫወተች ነው በማለት ያቀረበውን ሪፖርትተበዳዩን የመውቀስና ወንጀለኛውን በሰብዓዊ መብት ሽፋን የማዳን ተግባርሲል ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ አጣጥሎታል።

 

ለአምስት ወራት የቆየው የሰብዓዊ ተኩስ አቁም ስምምነት ፈርሶ ጦርነቱ ካገረሸበት ነሐሴ ወር ጀምሮ በትግራይ ላይ በተፈጸሙ የአየር ጥቃቶች በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የረድዔት ሰራተኞች ተናግረዋል።

 

በተጨማሪም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መስከረም 30 ባወጣው የውስጥ ሪፖርት መሰረት በግጭቱ ወደ 470 ሺህ ሰዎች እንደተፈናቀሉ የሮይተርስ ዘገባ ያስረዳል።

 

ጦርነቱ ማገርሸቱን ተከትሎ ሰብዓዊ እርዳታዎች የተስተጓጎሉ ሲሆን ይህም ሁኔታ አስከፊ የሆነውን የክልሉን የሰብዓዊ ሁኔታ ወደበለጠ ቀውስ ሊከተው እንደሚችል የረድዔት ድርጅቶች እየተናገሩ ነው

 

ባለፈው ሳምንት በአፍሪካ ህብረት አዘጋጅነት ሊደረግ ታቅዶ የነበረው የሰላም ውይይትየሎጂስቲክ ጉዳይበሚል ግልፅ ባልሆነ ምክንያት መራዘሙን ተከትሎ የፌደራሉ መንግሥትና የትግራይ ኃይሎች ወደ ውይይቱ ይመለሱ እንደሆነ ግልጽ አይደለም።

 

ነገር ግን በአሁኑ ወቅት በዋሽንግተን በሚካሄደው የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እና የዓለም ባንክ ስብሰባ ላይ እየተሳተፉ ያሉት የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር እዮብ ተካልኝበሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታትውስጥ የሰላም ድርድር እንደሚኖር ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል።

 

ምንጭ፡- ቢቢሲ

አስተያየት ይለጥፉ

0 አስተያየቶች